ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደ ማርያም ለአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ሽልማት በእጩነት ቀረቡ

ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደ ማርያም ለአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ሽልማት በእጩነት ቀረቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ፕሮፌሰር ሒሪት ወልደ ማርያም ለአፍሪካ ሕብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ተሰማ።

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ  ኢትዮጵያን በመወከል  ለአፍሪካ ሕብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ይፋ ሆኗል።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሒሩት ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋና የቋንቋ ጥናት ክፍል ለረጅም ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።

LEAVE A REPLY