ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአዲስ አበባ ከተማ ችግሮችን በጥናትና ምርምር ለመለየት እና ችግሮችን ለማረም አብሮ የመሥራት ዝግጁነት ቢኖረኝም ብዙዎቹ የአስተዳደሩ ቢሮዎች ፈቃደኛ አይደሉም ሲል የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ገለጸ።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነ መስቀል ጠና፤ ተቋማቸው በየመሥሪያ ቤቶቹ ያሉ የአገልግሎት አሰጣጥና የአስተዳደር ችግሮችን ለማረም የማኅበራዊ አገልግሎት ግዴታ አለበት ከማለታቸው ባሻገር፤ የአስተዳደሩ ቢሮዎችም ይህንኑ አውቀው የከተማን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለማረምና የተሳካ የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ መዘርጋት እንዲቻል የአብረን እንሥራ ጥሪ ቀርቦላቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለሥልጣን ያካሄዱትን ጥናት መሰረት አድርገው ለሰራተኞቹ ሲሰጡ ለብዙ ችግሮች መነሻ እና ለአገልግሎት አሰጣጥ ብልሹነት የሠራተኞች ክህሎት ማነስ አንዱ ሰበብ ነው ብለዋል።

























