ኢትዮጵያ በዳርፉር ሰላም ማስከበር የነበራት ሚና ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ በዳርፉር ሰላም ማስከበር የነበራት ሚና ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሂደት  ኢትዮጵያ በርካታ ወታደሮችንና የፖሊስ ኃይል ያሰማራችበት የዳርፉር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ተጠናቀቀ።

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ሥር በተለያዩ ሀገራት ውስጥ ለሚደረጉ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ የሚባለውን ከ8 ሺኅ 300 በላይ ሠራዊት የምታበረክት ሀገር ናት።
በምጽሀረ ቃል ዩናሚድ (UNAMID) ተብሎ የሚታወቀው በዳርፉር ሰላም ለማስከበር የተሰማራው ኃይል ከዚህ በኋላ በሱዳን እንደማይቀጥል የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት መግለጹን ተከትሎ፤ ምክር ቤቱ በሱዳን እና በዳርፉር ያለውን አንጻራዊ ሰላም፣ የሽግግር መንግሥቱ ከአማጺያን ጋር ያደረጋቸውን የሰላም ስምምነቶች፣ እንዲሁም አጠቃላይ ለውጦችን ከግምት በማስገባት እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY