በመተከል ዞን እየተወሰደ ባለው እርምጃ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን እየሰጡ ነው ተባለ

በመተከል ዞን እየተወሰደ ባለው እርምጃ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን እየሰጡ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፣ መተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር እርምጃ በርካታ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን ለጸጥታ ሃይሉ እየሰጡ ነው ተባለ።

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል፤ የህግ ማስከበርና የፀጥታውን ዘርፍ በበላይነት የሚመሩት ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ፤ የጥፋት ቡድኑ በመተከል ዞን በተለይም ቡለንና በቆጂ ወረዳዎች ዜጎችን በመግደል፣ ንብረት የመዝረፍና የማቃጠል አረመኔያዊ ተግባር ፈጽሟል ብለዋል።
የተጠናከረ ዘመቻ በማካሄድ በአካባቢው ህግ በማስከበር ሰላምን ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት በርካታ የታጠቁ ሃይሎች እጃቸውን እየሰጡ ነው ያሉት ጀነራሉ፤ ታጣቂ ቡድኑ ቀደም ሲል የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ስጋት አድሮባቸው መኖሪያቸውን ለቀው የነበሩ ዜጎችም ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY