ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህጋዊነት የተመዘገቡ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶችን ዛሬ ይፋ አደረገ፡፡
በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከጥር 13 እስከ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፓርቲዎች ምልክት የሚያስገቡበት እና ቦርዱ አጣርቶ የሚያፀድቅበት መሆኑ አይዘነጋም።
ይህን ተከትሎ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን እንደመረጡ እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደፀደቀ ቦርዱ አረጋግጧል።

























