ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ መወያየታቸው ተሰማ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጠናዊና ዓለም ዐቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ዓለምን እያስጨነቀ ስለሚገኘው ኮቪድ-19 ዙሪያ መወያየታቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ እና ጀርመን መካከል ያለውን የልማትና የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ እንደመከሩም ገልጸዋል።
ዛሬ በተለያዮ የኦሮሚያ ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ የተደረገላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለተደረገላቸው ድጋፍ የኦሮሚያን ሕዝብ አመስግነዋል።

























