ህወሓት ጣልያን ከ125 ዓመታት በፊት የሠራችውን ስሕተት ደግሞታል ሲሉ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ...

ህወሓት ጣልያን ከ125 ዓመታት በፊት የሠራችውን ስሕተት ደግሞታል ሲሉ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና እጅግ አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና በሀገር ላይ ክህደት የፈጸመው ህወሓት ጣልያን ከ125 አመት በፊት የፈጸመችውን ስህተት እንደደገመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ነገ ለሚከበረው125ኛው የዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ነው ይህንን እውነታ ላይ የተመረኮዘ ንግግር ያደረጉት።
የዐድዋ ዘመቻ ኢትዮጵያውያንን ከጥንቱ በተሻለ ያስተሳሰረ ዘመቻ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤  “ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው አደጋ ላይ የወደቀች መሆኑን ሲያረጋግጡ ሁሉን ነገራቸውን ትተው፣ በኢትዮጵያዊነታቸው ተግባብተው እንደሚዘምቱ አላወቀም። የሆነው ግን ይሄው ነበር” ሲሉም የቅርብ ጊዜውን የህወሓት ጁንታ ጥፋት እና የጣልያንን ስህተት አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY