ከሀሰተኛ ትርክት ያልተላቀቀው ብልፅግና በአደዋ በዓል ሀጫሉና ዐቢይ አሕመድን ሲያወድስ ዋለ

ከሀሰተኛ ትርክት ያልተላቀቀው ብልፅግና በአደዋ በዓል ሀጫሉና ዐቢይ አሕመድን ሲያወድስ ዋለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በመንግሥታዊ መዋቅር ላይ ሆኖ ከጽንፈኝነት እሳቤው መላቀቅ ያልቻለው የኦሮሚያው ብልፅግና ትናንት የአደዋ ድልን በተቃርኖ አክብሯል።

ካለፉት አምስት አመታት ወዲህ በድምቀትም በይዘትም እያደገ የመጣውን የአደዋ ድል በዓል መንግሥት ሳይፈልገው በግድ፣ በሕዝብ ግፊት እና ጫና እንዲከበር አስገድዶታል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፤ በተለይም አደዋ የአፄ ምንሊክ ሐውልት በሚገኝበት ስፍራ ሲከበር ቢኖርም፤ ትናንት ግን የብልጽግና ጽንፈኞች በመስቀል አደባባይ ሲያከብሩት ታይቷል።
በመስቀል አደባባይ የተካሄደው የአደዋ ድል በዓል ላይ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፈጽሞ አለመሳተፉንና አካባቢው ከተለያዮ የአዲስ አበባ ዙሪያ በመጡ ፈረስ ጋላቢዎች ተጥለቅልቆ ተመልክቷል።
የኦሮሚያ ብልጽግና ዛሬም በተሳሳተ የታሪክ ትርክት ውስጥ እየጦዘ እንደሚገኝ ባረጋገጠ መልኩ የአደዋ ድል መሠረት የሆኑትን አፄ ምንሊክ እና እቴጌ ጣይቱን ዘንግቶ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ሀጫሉ ሁንዴሳን ሲያወድስ ታይቷል።
ከመስቀል አደባባይ እስከ ስታዲየም እና ደምበል ሲቲ ሴንተር ድረስ አደዋን ለመዘከር ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶባቸው የተሠሩት እና የተሰቀሉት ፎቶዎች በተመሳሳይ የዶ/ር ዐቢይ እና የባልቻ አባ ነፍሶ ብቻ መሆኑ ደግሞ ብዙኃኑን አበሳጭቷል።
የአዳነች አቤቤ አስተዳደር ባዘጋጀው በዚህ ክብረ በዓል ላይ የኦነግ ባንዲራም በግልጽ ሲውለበለብ ታይቷል።

LEAVE A REPLY