ዳንኤል ክብረትን በ”ግል” ተወዳዳሪ ስም የአንዷለም አራጌ ተፎካካሪ ሆኖ አቀረበ

ዳንኤል ክብረትን በ”ግል” ተወዳዳሪ ስም የአንዷለም አራጌ ተፎካካሪ ሆኖ አቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና  በአዲስ አበባ ከተማ በብዙ መልኩ ድጋፍ የተነጠቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብልፅግና ፓርቲ ከወዲሁ የኢዜማ እና የባልደራስን ድምፅ ለመከፋፈል ጥረት እያደረገ ነው ተባለ።

   በሴራ ፖለቲካ የተካነው የቀድሞው ኢሕአዴግ የአሁኑ ብልፅግና ፓርቲ በቀጣዮ ሀገራዊ ምርጫ የአዲስ አበባን ነዋሪ ድምፅ ለመከፋፈል ሆን ብሎ የተለያዮ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑን ምንጮች ገለጹ።
   ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደ ገለጹት ከሆነ ብልፅግና ምንም ድጋፍ በሌለው በፈረንሳይ ለጋሲዮን፣ በጃንሜዳ፣ ምንሊክ፣ 6 ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እና በጠቅላላው በቀደሞ አጠራር ወረዳ 12/13 አካባቢዎች የሚወዳደረው የኢዜማው አንዷለም አራጌ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኑን ተከትሎ መንግሥት ስጋት ላይ ወድቋል።
አንዷለም አራጌ ባለፉት የህወሓት/ኢሕአዴግ የሥልጣን ዘመናት እንደ ወርቅ በእሳት የተፈተነ፣ ለሕዝብ እና ለሀገር ክብር ሲባል መከራና ስቃይን ያለ መታከት የተቀበለ መሆኑ በብዙኃኑ ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱን ታዛቢዎች ገለፀዋል።
አንዷለም አራጌን የሚገዳድር ሆኖ የቀረበው ደግሞ ከዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከፈተኛ ቁርኝት እንዳለው የሚታወቀውን ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት መሆኑ ብዙዎችን ጥርጣሬ ውስጥ ከቷል።
ሰባኪውና የታሪክ ጸሐፊው ዳንኤል ክብረት በብልፅግና ስም ለውድድር የመቅረብ ዕድሉ እንዳለ ሆኖ፣ በዋናነት የኢዜማና የባልደራስን ድምፅ ለመክፈል እየሠራ ያለው መንግሥታዊ ፓርቲ ለይስሙላ በግል ተወዳዳሪነትም ሊያቀርበው እንደሚችል እየተነገረ ነው።

LEAVE A REPLY