ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የመንግሥት ጸጥታ ሃይሎች የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበርየሆኑት የአቶ ዳውድ ኢብሳን መኖሪያ ቤት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደበረበሩ ኦነግ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ከትናንት በስቲያ ምሽት የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች ወደ ሊቀመንበሩ ቤት በማምራት የግቢውን ኤሌክትሮኒክ ኮምንኬሽን መሳሪያ በመበጠስ፣ በር ሰብረው እንደገቡ እና በቤተሰብ አባላት ላይ ድብደባ እንደፈፀሙ የገለፀው የግንባሩ መግለጫ፣ ከብርበራው በኋላ ኮምፒውተሮች፣ ስልኮች፣ ሰነዶች እና ኤሌክትሮኒክ ቁሳቁሶች መወሰዳቸውንም አመልክቷል፡፡

























