የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ መውጣት የዓለምን ትኩረት ስቧል!

የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ መውጣት የዓለምን ትኩረት ስቧል!

በትግራይ ጉዳይ አሜሪካ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራች!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና“ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ በመስዋትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን እናሳውቃችኋለን”
የአማራ ብልጽግና

የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ስትጠይቅ የቆየችው አሜሪካ፣ በትግራይ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ለማድረግ ለፀጥታው ምክር ቤት ጥሪ ማቅረቧ ተነግሯል።

ትና ንት ሰኔ 21/ 2013 ዓ.ም. የፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ማወጁን ተከትሎ፣ አሜሪካ አየርላንድ እና እንግሊዝ አስቸኳይ ስብሰባ የጠሩ መሆናቸው ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ ሀገራቱ የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እስከ አርብ ባለው ግዜ ስብሰባ እንዲቀመጥ ጥሪ ማቅረባቸውንም አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

በሌላ በኩል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት ሰኔ 21 ቀን ከተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር በስልክ መምከራቸው የተሰማ ሲሆን፣ በስልክ ንግግራቸው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ “ውጤታማ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ” ማለታቸውን አልጀዚራ አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የአሸባሪው ትህነግ አመራሮች በተደጋጋሚ ለደረሰባቸው አሳፋሪ ሽንፈት የአማራን ኢሊት ተጠያቂ በማድረግ ሂሳብ እንደሚያወራርዱ ነግረውናል። ትህነጎች የሚያወራርዱትን ሂሳብ ከአማራ ልሂቃን ጋር ያያይዙት እንጂ እውነታው ግን የአማራን ሕዝብ ስለማለታቸው ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለንም። ለዚህ ተጨባጭ ግምገማ አስረጅ ምሳሌው ትህነግ በታሪካዊ ጠላትነት የፈረጀው የአማራን ሕዝብ እንደአጠቃላይ እንጂ የአማራን ልሂቃን በለዬ ሁኔታ አይደለም። ስለሆነም የትህነጎች ሂሳብ ማወራረጃ የአማራ ሕዝብ እንጂ ልሂቁ ብቻ አይደለም። ይህ አዲሱ ማደናገሪያቸው ነው” ብሏል።

“ጥላቻቸው በአማራ ሕዝብ ላይ ነው። ስሁት ትርክት የፈጠሩት፣ ለዚህ ማስፈጸሚያ መዋቅር የነበሩት ልሂቁን ብቻ ሳይሆን አማራን እንደሕዝብ ለመጉዳት ሆነ ብለው አስበው፣ አቅደውና አጥንተው ነው። ጥላቻው የአማራ አርሶ አደር ጓዳ ድረስ የዘለቀ ነው። በተግባር ፈጽሞ የማይሳካ ቢሆንም በፕሮፖጋንዳ ደረጃ ዛሬ “ሂሳብ እናወራርዳለን” ሲሉ ቢሳካላቸው የአማራ አርሶ አደር ጓዳ ድረስ የዘለቀ የሰይፍ በትር የመዘርጋት ሰይጣናዊ ተነሳሽነት አላቸው። በትህነግ የሂሳብ ማወራረድ እሳቤ የሚዘረፈው ንብረት የአማራ ሕዝብ ንብረት ሲሆን፤ ሊደፈሩ የታሰበው ደግሞ የአማራ እናትና እህት ናቸው። ተገዳዩ ደግሞ ሁሉም አማራ ነው” ያለው መግለጫው “ዛሬ መላው የአማራ ሕዝብ በትህነግ ዳግም ሊሰነዘርበት የታሰበውን የጥፋት ሰይፍ በደንብ ተረድቶታል። የብሔራዊ ንቃት ስሜቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ አድጓል። የሞራል ልዕልና ከፍታውን ባለበት አስጠብቋል። በፍቅር ለመጣ በተለመደ ሰብዓዊ ጀግንነቱ እጁን ይዘረጋል፤ በጥላቻ ለሚመጣ ተገቢውንና የማያዳግም ትምህርት ሰጥቶ ይመልሳል” ሲል ገልጿል።

ፓርቲው በዚሁ መግለጫው “የአማራ ሕዝብ የትኛውንም በቀል ለመበቀል ፍፁም አልተዘጋጀም። ይህ ማለት ግን “ሂሳብ እናወራርዳለን” ባዮችን በዝምታ ይታገሳል ማለት አይደለም። ከዳተኛና ጸረ-ሕዝብ የሆኑ የትኞቹንም ጠላቶቹን ያለ ምህረት ይታገላል። ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ በራሳቸው መስዋትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናሳውቃችኋለን። እነዚህን አካባቢዎች ደግሞ ከሕግ ውጭ በጉልበት ወስዶ ለመጠቅለል ፍላጎት ካለ፣ ለነፃነቱ ሲል ዋጋ የማይከፍል አማራ የሌለ መሆኑን ደግመን ደጋግመን እናረጋግጥላችኋለን” በማለትም ወቅታዊ አቋሙን አሳውቋል።

LEAVE A REPLY