ኢትዮጵያና እስራኤል በኢንቨስትመንት የድጋፍ ስራዎችን በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ

ኢትዮጵያና እስራኤል በኢንቨስትመንት የድጋፍ ስራዎችን በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜና ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ የሁለቱን አገራት የቆየ የኢንቨስትመንት ግንኙነት አጠናክሮ ስለመቀጠል፣ በጋራ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለእስራኤል ባለሀብቶች ማስተዋወቅ በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም በኢንቨስትመንት ዘርፉ የድጋፍ እና ክትትል ስራዎችን በጋራ መስራት እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ መሳተፍ በቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

LEAVE A REPLY