ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የደቡብ ሱዳን ህዝብና መንግስት ሁልጊዜም ታማኝ ናቸው ሲሉ የሀገሪቱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለሆኑት አቶ ነቢል መህዲ ገልፀዋል።
በሪክ ማቻር እና አምባሳደር ነቢል ግንኙነት እንደተገለፀው ደቡብ ሱዳን ለኢትዮጵያ ሰላም ቁርጠኛ በመሆኗ ከደቡብ ሱዳን ምንም አይነት ኢትዮጵያን የሚጎዳ ተግባር አሁንም ወደፊትም አይኖርም መባሉን የኢፌዴሪ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር እና በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መህዲ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ተብሏል።
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለዉ ጦርነት ጋር በተያያዘ በጎረቤት ሀገራት በኩል የታጣቂ ኃይሉ ህወሓት ሙከራዎችን ማድረጉ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት እንደተገለፀ የሚታወስ ነው።

























