ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዘመን ባስ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖችን በነፃ ትራንስፖርት ወደ ቀያቸው መመለስ ጀመረ፡፡
ዛሬ በሁለት አውቶቡስ የጀመረው አገልግሎቱ ለ10 ቀናት እንደሚቆይ ድርጅቱ ገልጿል፡፡
የዘመን ባስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አይላቸው አያና በአዲስ አበባ እና በሌሎች ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ የደሴ፣ የኮምቦልቻ፣ የሸዋሮቢት፣ የከሚሴ እና ሌሎች ነጻ የወጡ አካባቢ ወገኖችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ነፃ ትራንስፖርትን አቅርበናል ብለዋል።
በአገልግሎቱ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለእናቶች እና ለህፃናት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ያስታወቁት ኃላፊው በርካታ ወገኖች እየተዘመገቡ ነው ብለዋል፡፡