/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በወልዲያ ከነማ እግር ኳስ ቡድን ላይ ተጥሎ የነበረው ቅጣት ተሻሻለ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወልዲያ ከፋሲል ከተማ ጋር ባለፈው ወር መጀመሪያ በአላሙዲ ስታድየም ጫወታ ሲያካሂድ፤ የወልዲያ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባት ግጭት ፈጥረዋል በማለት ለፋሲል ከተማ ፎርፌ እንዲሰጥ፣250 ሺህ ብር ቅጣት፣ ቀሪ የሜዳው ጨዋታዎችን ከወልዲያ በ500 ኪሜ ርቀት እንዲያደርግ፤ በመሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስታድየም ለአንድ ዓመት ጫዋታ እንዳይካሄድና በአሰልጣኝና ተጫዋቾች ላይ ቅጣት መጣሉ ይታወቃል።
በመሆኑም የወልዲያ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት ፌዴሬሽኑ ቅጣቶችን አሻሽሏል።
250 ሺህ ብር የነበረው የገንዘብ ቅጣት ወደ 150 ሺህ ዝቅ እንዲልና 3 ጫዋታዎችን ብቻ ከሜዳው ውጭ እንዲጫወት መወሰኑ ታውቋል።