ጠ/ሚር አብይ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ እያነጋገረ ነው

ጠ/ሚር አብይ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ እያነጋገረ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጡ።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለጥያቄ በጠራቸው መሰረት በቦታው ተገኝተው ከ2፡30 በላይ የወሰደ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩን ማብራሪያም በርካታ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ሲከታተሉ ተስተውለዋል። ETV, OBN, Fana, Walta, Debub Tv, Amhara Tv ሪፖርቱን በቀጥታ ያስተላለፉ ሲሆን Tigray Tv የመቀሌ ከነማንና የመከላካያ ቡድኖችን ጨዋታ በድጋሜ ማስተላለፍ ታውቋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ለፓርላማ አባላት አጭር ሪፖርት ካቀረቡ በሗላ የተለያዩ ጥያቄዎች ከም/ቤቱ አባላት ቀርቦላቸዋል።ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስለወሰናቸው የባድመ ጉዳይ፣ግዙፍ የመንግስት የንግድ ተቋማት ወደ ግል ይዞታ ለማዞር አክሲዮን ለመጨጥ የወሰነበትን፣ሰሞኑን በስፋት ስለተከሰተው የዜጎች መፈናቀልና የርስ በርስ ግጭት እንዲሁም ስለ ፖለቲካ እስረኞች ፍች የተመለከቱ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የአልጀርሱን ስምምነት ህዝብ ሳይወያይበት መቀበሉንና ውሳኔ ቀድሞ ለህዝብ መገለፅ አልነበረበትም ተብለው ለተጠየቁት፦ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲመልሱ “ከዚህ በኃላ የስራ አስፈፃሚ ስብስባ በየሰዓቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይገለፃ።ከዚህ በኃላ ከኢትዮጵያ ህዝብ  በድብቅ የሚደረግ የፖለቲካ ውይይት አይኖርም ።በግርድፉ እንለቃለን።አብረን እናብሳላለን።” በማለት መልሰዋል።

 ጠቅላይ ሚንስትሩ አያይዘውም “አሰብን ስንሰጥ መቼ ህዝብን አወያይተናል….?ለአሰብም የሞተው የኢትዮጵያ ልጅ ነው።”በማለት ስሜት በተቀላቀለበት መንገድ ለም/ቤቱ መልሰዋል።

የአልጀርሱን ስምምነት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከዚህ ቀደም ተቀብሎ ማስፀቁንና አቶ መለስ ዜናዊም ለአፍሪካ ህብረት ማሳወቃቸውን ጠቅሰው በባድመ ጉዳይ እርሳቸውም ምንም አዲስ ነገር እንዳላመጡ ወይም እንዳልወሰኑ ገልጸዋል።ነገር ግን በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን የፖለቲካ ለውጥ ያልደገፉ አንዳንድ አካላት ነገሩን ሆን ብለው በማጣመም ለርካሽ ፖለቲካዊ ትርፍ ለመጠቀም እየተሯሯጡ መሆኑ ጠቁመዋል።

ወንጀል የፈፀሙ አካላት እየተፈቱ በመሆኑ “የሽብር አዋጁ ተጥሷል” ለሚለው ጥያቄም፡

ጠ/ሚኒስትር አብይ “ሽብር ምንድን ነው? ሽብር በስልጣን ለመቆየት ሀይልን መጠቀምን ይጨምራል! ……ህገ መንግስቱ ግረፉ፣ ጨለማ ቤት አስገቡ ይላል? አይልም። መግረፍ፣ ጨለማ ቤት ማስገባት የእኛ የሽብር ተግባር ነው።ለዚህም ይቅርታ ጠይቀናል።”ብለዋል።

በመንግስት የተያዘዙን ትላልቅ ተቋማትም የተወሰነ ፐርሰንት ወደ ግል እንዲዞር ያስገደዳቸውን ምክንያት አብራርተዋል።እንደ ጠ/ሚኒስትሩ ገለፃ ትላልቅ ተቋማት የተወሰነ ፐርሰንት ወደ ግል እንዲዞር ያስገደዳቸው፤ ሀገሪቱ ስትበደር ኖራ ብድር መመለስ ባለመቻሏ፣የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን መጀመር እንጂ መጨረስ ባለመቻላቸው፣የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መምጣቱና ስራ አጥ ዜጎች እየተበራከቱ መምጣቱ እንደ ዋና ምክንያት አስቀምጠዋል።ይህም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያሻውና ጊዜ የሚወስድ ነገር መሆኑን ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY