ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለመከላከያ ሀይልና ለፌዴራል ፖሊስ አባላት ዝዕዛዝ ሰጡ

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለመከላከያ ሀይልና ለፌዴራል ፖሊስ አባላት ዝዕዛዝ ሰጡ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ግጭት በሚያስነሱ አካላት ላይ የመከላከያ ሀይልና የፌዴራል ፖሊስ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እርምጃ እንዲወስዱ ሲሉ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኤርትራውን ፕሬዚዳን ሸኝተው ዛሬ ጠዋት በሰጡት መግለጫ በኢትዮ_ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው ብለዋል። በዚህም  በቀጥታ በሚሳተፉ ብቻ ሳይሆን ራቅ ብለው ክብሪት የሚያቀብሉ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በድጋሜ አስጠቅቀዋል። በደቡብ፣ በሰሜን የእየታዩ ያሉ ህዝብ ከብዝብ የሚያጋጭ አካሄድ አሁን ለጀመረነው ጉዞ እንደማይጠቅምና ሁላችንም ተደምረን የላቀ ቀጠና መፍጠር እንጂ ጊዜው ያለፈበት የመነጣጠል አጀንዳ ጊዜው አልፎታል ብለዋል።

የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም ቀጠና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭና ህይወት በሚያጠፋ ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖችን ለህግ እንዲያቀርቡ በማለት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። የፀጥታ ሀይሎች ይህን ሲያደርጉም የሰው ህይወት እንዳይጠፋና ተጨማሪ ጉዳት አንዳይደርስ የሀገራዊና ህገ_መንግስታዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

የኦሚያና ሶማሌ ክልል አመራሮችም ተገናኝተው ስለሁኔታው እንዲመክሩ አዘዋል።

በአሁኑ ወቅት ኦሮሞ ከሶማሌ፤ አማራ ከኦሮሞ፣ ሲዳማ ከወላይታበሰላም አብረው እንዳይኖሩና እንዲጋጩ የሚፈልጉ ጥቂት ሰዎች ከዚህ ከዚያም እንዳሉ ጠቁመዋል። የፌዴራል መንግስት ግጭቱን አንደሚያረጋጋና ለህዝብም አንደሚያሳውቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የውጭ ምንዛሪ በእጃቸው የያዙ አካላት በፍጥነት ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ከጥቂት ሳምንታት በሗላ በተከማቹ የገንዘቦች ላይ ዘመቻ (ኦፕሬሽን) እንደሚጀመርም አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY