ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአንድ ዓመት የስልጣን ዘመናቸው ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት ሲያደርጉ የቆዩት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ ሀሙስ ግንቦት 28 ቀን 2011 ከፍትህ አካል አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከመላ አገሪቱ ከተውጣጡ የፍትህ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ያደረጉት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ በዚህች ሀገር ላይ ሕዝብ በህግ ፊት እኩል መዳኘት እንደሚገባው አሳስበዋል:: ሙያተኞችም ቃል ኪዳን በገቡት መሰረት ህግን የተመረኮዘ ግልፅና እውነተኛ አሰራርን መሰረት ባደረገ መልኩ ፍትህን በተገቢው መንገድ ማስፈን እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ከ3ሺህ በላይ ዳኞች ዐቃብያን ሕግ፣ ጠበቆችና የፍትህ ዘርፍ አመራሮች እንደሚገኙ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የመጣው መረጃ አመላክቷል፡፡

























