ብሔርተኝነት የነገሰበትና ከኳሱ ይበልጥ “ፀቡ ያደገው” የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋረጠ

ብሔርተኝነት የነገሰበትና ከኳሱ ይበልጥ “ፀቡ ያደገው” የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋረጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ብሔርተኝነት የነገሰበት፣ ከኳሱ ይበልጥ “ፀቡ ያደገው” የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋረጠ በጸብና በግርግር የታጀበው የኢትዮጵያ የወንዶች ፐሪምየር ሊግ ውድድር ሊገዜው እንዲቋረጥ የፌደሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ በጸጥታ ስጋት ምክንያት አልተካሄደም::

ይህንን ተከትሎ ዛሬ ሀሙስ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሄደው ስራ አስፈጻሚ ሁለቱ ቡድኖቹ በአዳማ ከተማ አበበ በቂላ ስቴዲየም ያለ ተመልካች በዝግ ስታዲየም እንዲጫወቱ አስቀድሞ የወሰነውን ውሳኔ መሻሩን ይፋ አድርጓል፡፡

ስራ አስፈፃሚው ከዚህም ባሻገር ቀጣይ የፐሪሚይር ሊግ ውድድሮች በተገቢው ሁኔታ እንዲካሄዱ፣ ከክለቦችና ባለድርሻ አካላት ጋር ተነጋግሮ ዘላቂ መፍትሄ እስከሚያበጅ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ መወሰኑ ታውቋል:: ተጨማሪ ወጪዎችንና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ የሚቀርቡ ማናቸውንም ጥያቄዎች በፌደሬሽኑ የዲሲፕሊን የውድድር ደንብ መሰረት በሂደት እንደሚታይ ገልጿል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልል ከተሞች የሚካሄዱ ውድድሮች ላይ የብሔርተኝነት መንፈስ በመንገሱ ደጋፊዎች በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት ኳሱን ትተው በስታዲዮሞች ውስጥ ወደ ጸብና ብሽሽቅ ውስጥ የተገባበት ሁኔታ በስፋት ሲታይ ቆይቷል፡፡ ከኳሱ ይልቅ ጸቡ ያደገው የኢትዮጵያ የወንዶች ፕርሚየር ሊግ በዚህ መልክ መቋረጡ በርካታ ስፖርት አፍቃሪያንን በእጅጉ ኣሳዝኗል፡፡

LEAVE A REPLY