ዛሬ በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግስት ከተሾሙት 21 ሚኒስቴሮች ውስጥ ስለሶስቱ (3)ለመጻፍ ፍልጌ ነበር። ትዝ ሲለኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለካ መንግስታችንአይደለም ብሏል። እንግዲያውስ “የጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መንግስት” ልበለው አልኩኝ። ቆም ስል ለካ የኃይለ ማርይምም መንግስት አይደለም። የጠቀለለው ነገር የለማ።ለዚህ የሾመባማቸው ሳይሆኑ ያልሾመባቸው ቦታዎች” እዩን! ስሙን!” ብለው በአደባባይ ይናገራሉ። የመከላከያሚኒስቴር፤የገንዘብ ሚኒስቴር፤የመገናኛ ሚኒስቴር።፣ የሕዝብ ደህንነት ሚኒስቴር፤የእርሻ ሚኒስቴር አልተነኩም። በነበሩበት ረገትዋል።መንግስትእንደሚያምነውም እነዚህ የሚነስቴር መስርያ ቤቶች “የኪራይ ሰብሳቢዎች!” ጠቅላይ መመርያ ናቸው። ሞተሩም መዘውሩም ያለው እዚያው ነውና።የኪርራይ ሰብሳቢ ማለት መለስ ዜናዊ ያመጣብን የፈረንጅ ቅኔ መሆኑ ነው። ቅኔው ሲፈታ “ዘራፊ!” ማለት ይመስለኛል። ይመስለኛል ያልኩት የተሻለ ትርጉምካለ ብዬ ክፍት ቦታ ለመተው ነው።