የኢትዮጵያ አውሮፕላን በቤይሩት ታግቶ ነበር

የኢትዮጵያ አውሮፕላን በቤይሩት ታግቶ ነበር

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ዛሬ ሀሙስ ማለዳ በቤሩት ራፊች አል ሀሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ  በሊባኖስበበረራ ድህንነቶች ተገዶ ለስአታት መታገቱ የሊባኖስ የሲቪል አቪዬሽን ጄኔራል ዳይሬክቶሬት አስታወቀ። 

ዳይሬክቶሬቱ በመግለጫው እንዳረጋገጠው የኤርፖርቱ ደኅንነት  አባላት በአውሮፕላኑ አካል ላይ በትናንሽ ፊደላት “ቴል አቪቭ” የሚለውን ከሩቅ ለማየት በጣም አስቸጋሪ የሆነ ፅሁፍ ተፅፎበት ስለአገኙ ነው ለሰአታት አግተውት የነበረው ። 

የኢትዮጵያ  አየርመንገድ ኩባንያ አውሮፕላኑን ከገዛ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፈበትን ኤርፖርት ስም መመዝገብ የተለመደ አሰራር ምክንያት ነው  በአውሮፕላኑ ላይ ቴልአቪቭ የሚለው ፅሁፍ የተፃፈው ሲል አብራርቷል። 

ኩባንያው አውሮፕላኑን ወደ ቤይሩት-ራፊክ አል ሃሪሪ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከማምጣቱ በፊት ይህንን ጉዳይ እንዳላስተዋለ ጠቁሟል። 

የሊባኖስ ሲቪል አቬሽን ጄኔራል  ዳይሬክቶሬቱ ኩባንያው አውሮፕላኑ ከቤይሩት እንዲነሳ ከመፍቀዱ በፊት ከአውሮፕላኑ ላይ  የተፃፈውን ሐረግ እንዲያነሳው ጠይቋል። 

የኢትዮጵያን አይርመንገድ  በቤሩት አውሮፕላን ማረፊያ ከማረፍዎ በፊት በኩባንያው አውሮፕላኖች ላይ ከአንድ እስራኤላዊ አካል ጋር የተያያዘ አርማ እንዳይኖር አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ  የሊባኖስ ሲቪል አቬሽን ጄኔራል  ዳይሬክቶሬቱ ጠይቋል።(enኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY