እኛ በኛ እንኩራ /ታዛቢው/

እኛ በኛ እንኩራ /ታዛቢው/

እኛ በኛ እንኩራ /ታዛቢው/

እንደ ትላንትናው፣ እንዳባቶቻችን
ከመሃል ከተማ፣ እስከ ጠረፋችን
ካመፀኞች ጋራ፣ ይጀመር ፍልሚያችን
ምንሽር ጓንዴውን፣ ያጩኸው ህዝባችን።

አገሬ ኢትዮጵያ፣ ቴዎድሮስ ያደገባት
ጋራው ሸንተረሩ፣ ታሪክ የሰራባት
ሜዳ መስሎት ዛሬ፣ ባንዳው ፈነጨባት።

ሞቅ ሞቅ አድርገው፣ ወያኔ ይሸበር
ትንፋሽ አሳጥረው፣ በማሰው ይቀበር።

ለእናት ኢትዮጵያ፣ ባንድነት ዝመቱ
ትርጉም አልባ፣ እንዳይሆን አገሬ ማለቱ
ግዴታን መወጣት፣ ይሁን እንደጥንቱ
ሬሳን ይመስል፣ ይብቃ መጨመቱ።

ሁሉም ጦሩን ያንሳ፣ ጠላት ላይሆን ወዳጅ
ሉአላዊነቱን፣ ያስከብር በግዳጅ።

ጀግና የጀግና ልጅ፣ የሃገር አለኝታ
ግንባሩን የሚሰጥ፣ ሳይፈራ ላንዳፍታ
ና ግጠመኝ የሚል፣ ሞልቶ በየቦታ
ውድ የሚሞትላት፣ አገሬ መች አጥታ።
ህጻን ሽማግሌ፣ ወጣት ወንድ ሴቱ
ዝናን ያተረፈ፣ ዛሬም እንደጥንቱ
ባገሩ የሚኮራ፣ ቆፍጣናና ብርቱ
ችግር የማይፈታው፣ የጥንት የጠኋቱ
ንቅንቅ የማይለው፣ ቆርጧል አንዴ ሃሞቱ።

ያሳለፍነው ይብቃ፣ ጠንክረን እንስራ
ሸክማችንም ይቅለል፣ እኛ በኛ እንኩራ
ንፋስ ሳይገባብን፣ ባንድነት በጋራ
ፋኖው ተነስና፣ ጓዶችህን ጥራ
ልክህን አሳየው፣ ለባንዳው ኩታራ።

LEAVE A REPLY