እንብላው !!! /ማህሙድ እንድሪስ/

እንብላው !!! /ማህሙድ እንድሪስ/

በየራሱ መንገድ ሁሉም በየግሉ
ከጧት እስከማታ ሲደክሙም ቢውሉ
ፍሬ አልባ ሆነና ፍለጋቸው ሁሉ
የለት ጉርሳቸውን ማግኘት ስላልቻሉ
አንበሳ ፣ ነብር ፣ ጅብ
በጋራ ለማደን ተስማምተው ወጡ አሉ ።

ሆኖም ብዙ ደክመው አንዳችም ስላጡ
ወዳመሻሹ ላይ ተስፋ እንደቆረጡ
ድንገት ቢያማትሩ ተራራው ጥግ ጋ
ከበቂያቸው በላይ ተከምሯል ስጋ
ግና ምን ያደርጋል
ሽታው አያስጠጋም በጣም ይጠነባል
እንኳን አፍ ሊገባ ላፍንጫም ያሰጋል ።

ከርሀቡን ጋራ እየተታገለ
አያ‘ንበሳም አለ
“ይህንስ ብንበላ
ወዲያው ይገለናል
ገና እንደጀመርነው ሆዳችን ሳይሞላ ።
ይልቅ ተጠናክረን እንፈልግ ሌላ ”

ነብርም ቀጠለ
ራቡን ለመቻል እየተጣጣረ
ሀሳብ ሰነዘረ
” ያገኘነው ምግብ
ሻግቶ ተበላሽቶ በጣም ስለገማ
አያ‘ንበሳ እንዳለው
እስኪ ሌላ እንፈልግ” በማለት ተስማማ ።
አያ ጅቦ ደሞ ሲናገር በተራው
“ያው እንደምታውቁት
ርሀብ አደንዝዞን ጠፍቶብናል መላው

እንግዲህ ምን ይደረጋል

እንብላም ብትሉ እንብላው ።

አንብላም ብትሉ እንብላው ።

LEAVE A REPLY