አንድነት ጠፍቶ ነው እንጂ ወያኔ ከወደቀ ቆይቷል /ከተማ ዋቅጅራ/

አንድነት ጠፍቶ ነው እንጂ ወያኔ ከወደቀ ቆይቷል /ከተማ ዋቅጅራ/

በይፋ የወያኔ መውደቅ የተጀመረበት ቀን የ1997 የምርጫ ግዜ ነው ። ህዝቡ ከዳር እስከዳር በመውጣት ህውአትን እንደማይፈልግ ያሳወቀበት ግዜ ነበረ። በነጻነት እና በዲማክራሲያዊ ስርአት ኢትያጵያን ሊመራ የሚችልን መሪ በመፈለግ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ መሪዋችን ለመምረጥ የማይፋቀውን የሁል ግዜ አሻራውን ያስቀመጠበት ግዜ ነበረ። ህውአቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ከነሱ ጋር አለመሆኑን ያወቁበት ብቻ ሳይሆን መቼም ሊመርጣቸው እንደማይችል የተረዱበትም ቀንም እንጂ። ከዛን ግዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ድህነት በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ፣ ያለፍርድ የሚታሰረው በዛ፣ በሰላም እጦት ከሚወዳት አገር የሚሰደደው በዛ፣ ለምን እኛን አልደገፍክም ተብሎ በግፍ የሚገደል በዛ፣ በአገራችን ላይ ሰቆቃው እየከፋ በመምጣቱ ወደመጨረሻው ምእራፍ የሚወስደን ግዜ ላይ ደርሰናል።

ህውአትና፣ ደጋፊዎችና አጫፋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ የሰራችሁት ስራ ወደ ፍጻሜው ጫፍ ደርሷል። እንግዲህ አሁን ማን እንደሚጎዳና ማን እንደሚጠቀም እድሜ የሰጠው ሁሉ ሊመለከተው ነው። የመከራ እና የጭንቅ ግዜዋ የትኛው ወገን ላይ ጸንቶ እንደሚዘልቅ ግዜ ፈራጁ የመጨረሻ ሰዓት ላይ አድርሶናል። ያዘነም ይስቃል፣ የሳቀም ያዝናል፣ ከፍ ያለም ዝቅ ይላል፣ ዝቅ ያለም ከፍ ይላል፣ የጨለመበት ይነጋለታል፣ የነጋለትም ይጨልምበታል፤ የሚለው የፈጣሪ ቃል ሊፈጸም ግዜው ደርሷል። ምክንያቱም ሁሉም ዋጋውን የሚያገኘው በሰራው ስራ መጠን ነው። ኩርችት የዘራ ኩርችትን ፍቅር የዘራ ሰላምን ያጭዳልና ነው።

ህውአት ከኢትዮጵያ ህዝብ ልቦና ውስጥ ከወጣ ሰነባብቷል ግና ምን ያደርጋል በአገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩ ከአገርና ክህዝብ ክብር ለሆዳቸውና ለጥቅማቸው ያደሩ ግለሰቦች ህዝባችንን በማለያየትና በማዘናጋት ስራ ላይ ተጠምደው የህውአትን ስራ ይሰራሉ። በዚህ ምክንያት እርስ በራሳችን የጎንዮሽ ስንራገጥ በቃላት ስንፋጅ የህውአት የግፍ አገዛዝ እየጨመረ የህዝባችን ዘግናኝ መከራ እየከፋ መጣ። ለህዝብ አስባለው የሚል ፖለቲከኛ ሁሉ ትግሉን ወደአንድት ትግል መግባት አለመፈለጋቸው ለህውአታውያን የእድሜ ማራዘሚያ ኪኒን የመስጠት ያህል ሆኖ ግፍአዊ አገዛዙን የሚጨምርለት ነው።

ህውአት በሽታው እንደ ካንሰር የማይድን ስለሆነ ግዜው ሲደርስ እንደሚሞቱ ቢያውቁም ባላቸው ሃይል ሁሉ እርስ በእርስ የማፋጀቱን ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። የሚያሳዝነው ግን ለሆዳቸውና ለጥቅም ብለው ህውአት በሽታው እንደ ካንሰር የማይድን ስለሆነ ግዜው ሲደርስ እንደሚሞቱ ቢያውቁም ባላቸው ሃይል ሁሉ እርስ በእርስ የማፋጀቱን ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። የሚያሳዝነው ግን ለሆዳቸውና ለጥቅም ብለው የወገኖቻችን ደም እንዲህ በየሜዳው ሲፈስ ህዝባችን ለታላቅ መከራና ሰቆቃ ሲዳረግ እያዩ አሁንም የህውአት አገልጋይ በመሆን የመከፋፈሉን ስራ በመስራት የኢትዮጵያ ህዝብ መከራ የማይሰማቸው ከህውአት ቀጥለው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት መሆናቸውን ሊያውቁት ይገባል። እንፋረዳቸውማለን።

አሁን ግን በግድ ተገፍቶ 100 ሚሊዮን ህዝብ ፓለቲካን እዲያውቅ በመደረጉ (ይሄ በራሱ ከባድ አደጋ ነው) እናም ሁሉን ነገር እየተረዳና እየተገነዘበ ስለመጣ የውስጥም የውጪውኑም ጠላት ስላወቀ ለነጻነት የመታገሉን ስራ በህዝብ መሪነት ትግሉ ከእለት ወደ እለት ስልቶችን እየቀያየሩ ለህውአት አልገዛም ባይነቱን እያሳየ ነው። ህዝባችን የመጨረሻውን ቃል ለአንባ ገነኖች አልገዛም ባይነትን በመንገር ወደ አደባባይ በመውጣት ዳውን ዳውን ወያኔ በማለት የህውአት አገዛዝ ማብቂያ ዋዜማው ላይ እንዳለ እያየን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ቀዩን መስመር አልፋል 11ኛው ሰአትም አልቋል የነጻነት መምጫው ግዜው ደርሷል። ከዛ በፊት ጥቂት መሰዋትነት አለ፣ ጥቂት መውደቅ ከዛም መነሳት ይመጣል የነጻነትም ፋናት በኢትዮጵያ ምድር ስትበራ ነጻነታችንን ያሳጡን ከነ ግብር አበራቸው ያኔ ዋጋቸውን ለመቀበል ከፊት ቀድማ ትጠብቃቸዋለች።

ሳጠቃልለው እናንተ የህዝብ አካል የሆናችሁ ለጥቅም ብላችሁ ህዝብን የመከፋፈል ስራችሁን አቁማችሁ የአንድነት ጥሪ በማቅረብ ለህዝባችን የታሰበውን የመከራ ዘመን በማሳጠር የነጻነታችን ግዜ እንዲፋጠን ታደርጉ ዘንድ የመጨረሻ እድል አላችሁ ይህ ሆኖ ባይገኝ ግን እናንተም የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት እንደሆናችሁ ልታውቁት ይገባል።

LEAVE A REPLY