በኢትዮጵያ የባንክና ቴሌኮም የንግድ ዘርፍ አሁንም የመንግስት ብቻ ሆኖ እንደሚቀጥል ተገለጸ

በኢትዮጵያ የባንክና ቴሌኮም የንግድ ዘርፍ አሁንም የመንግስት ብቻ ሆኖ እንደሚቀጥል ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢትዮጵያ መንግስት ጠቅልሎ (በሞኖፖል) የያዘውን የባንክና ቴሌኮም የንግድ ዘርፍ አሁንም ወደ ግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ለማሻገር ዝግጁ አለመሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዛሬ ገለጹ።

በፖላንድ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ርዕሰ ብሔር ሙላቱ ተሾመ ሀገራቸው በቴሌኮም (ስልክ) የንግድ መስክ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ባለሀብት ዝግ ሆኖ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በኢንደስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ ለመሳተፍ ለሚፈልግ ባለሀብት በሩ ክፍት መሆኑንና በተለይም በግብርና፣ ቆዳ፣  መድሀኒት፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ምግብና ሻይ ምርት ለሚሰማራ ኢንቨስተር መንግስታቸው ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የቴሌ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመንግስት ስር የወደቀ ሲሆን ባንክ ደግሞ ለሀገር ውስጥ ብቻ የተፈቀደ ውስንነት ያለበት ዘርፍ መሆኑ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY