ባህር ዳር በጫት ምርት ላይ ቀረጥ ልትጥል ነው ተባለ

ባህር ዳር በጫት ምርት ላይ ቀረጥ ልትጥል ነው ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የባህር ዳር ከተማ አስተዳድር ገቢዎች ጽ/ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው ከነገ ሚያዚያ 17/2010ዓ.ም ጀምሮ በጫት ምርት ላይ ቀረጥ እንደሚጥል አስታውቋል።

የከተማው የገቢዎች ጽ/ቤት ጨምሮ እንደገለጸው በጫት ምርት ላይ ቀረጥ መጣል ያስፈለገበት ምክንያት፣ “የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የገዥን አቅም ማዳከምና ጫት የሚቅም ወጣትን ለመታደግ የታሰበ ነው።” ብለዋል፡፡ በሌላ በኩልም ለከተማው ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡

በቅርቡ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት ወደ ባህር ዳር ከተማ በቀን ከ5ሺህ ኪ.ግ በላይ የጫት ምርት እንደሚገባ ተገልጿል።

በዚህ መሰረት ለባህር ዳር አካባቢ ከ1 ኪ.ግ ጫት ላይ 5 ብር ቀረጥ የተቀመጠ ሲሆን ከባህር ዳር ውጭ በሚጫኑ የጫት ምርቶች ከ1 ኪ.ግ የጫት ምርት ላይ 30 ብር የተቀመጠ መሆኑን የአማራ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

LEAVE A REPLY