/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በቅርቡ ከእስር ቤት የወጣው ጋዜጠኛና የመብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ቢሮ መክፈቱን ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል ገለጸች። ከሰባት ዓመታት እስራት በሗላ ባለፈው የካቲት ወር ከቃሊቲ እስር ቤት የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይት ሲያካሂድ ቆይቷል።
ከአራት በላይ አለም አቀፍ ሽልማቶች ያገኘው እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ ፕሬስ ታሪክ የጎላ ድርሻ እንዳለውም ይታወቃል። እስክንድር የሚዲያ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ መክፈቱን በማስመልከት ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል በፌስ ቡክ ገጿ የሚከተለውን አስፋራለች።
_____________
“እስክንድር ነጋ የሚዲያ ቢሮ ከፈተ! ላለፉት 12 አመታት በህወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ። በቅርቡም በተለያዩ የሚዲያ ውጤቶች ከህዝቡ ጋር ለመገናኘት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል…..ጋዜጠኞች ተሰባስበውም ኬክ በመቁረስ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል….ነፃው ፕሬስ ታፍኖ አይቀርም….የህዝብ አደራ አለብን! ድል ለዲሞክራሲ!”