/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ዕርቀ ሰላም መፍጠሯን ተከትሎ ብጹዕ አቡነ መርቆሮዮስ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ነገ ከቀኑ 6 ሰዓት አዲስ አበባ ይገባሉ ተባለ። አዲስ አበባ ሲደርሱ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ድረስ የአቀባበል ስነ_ስርዓት ይካሄዳል ተብሏል።
ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስና ብፁዕ አቡነ ማትያስ የሚታደሙበት የዕርቀ ሰላም ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 28/2010 በሚሌኒየም አዳራሽ የዕውቅና ፕሮግራም ለማዘጋጀት መርሃ-ግብር መያዙ ታውቋል።በዝግጅቱ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ 25 ሺህ ሰዎች እንደሚታደሙበት ተገልጿል።
በሀገር ቤት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ላለፉት 27 ዓመታት በውጭ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፏቸው የነበሩ ውግዘቶችን ማንሳቱን ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።