የፋሽሽቱ ናዚ ህ.ወ.ሓ.ት.ገበና ጥቁር ታረኩ ክፍል አንድ /ከገብረመድህን አርአያ-አውስትራሊያ/

የፋሽሽቱ ናዚ ህ.ወ.ሓ.ት.ገበና ጥቁር ታረኩ ክፍል አንድ /ከገብረመድህን አርአያ-አውስትራሊያ/

ሓምሌ 20/2010 ይህ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ማንነት የሚያጋልጥበት 23 ክፍሎች ያቀፈ በተከታታይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚቀርብ ሰነዶች ነው።

ክፍል አንድም እንሆ // ህ.ወ.ሓ.ት. ፋሽሽታዊ አፓርታይድ ዘረኛ ስርአት ‘’የኔ መንገድና ፖሊሲ የማይቀበል ጠላት ነው ‘’ብሎ በሚከተለው ኋላ ቀር ርዕዮተ ዓለሙ፤ በንፁሃን ኢትዮጵያውያን ደም የታጠበ ፋሽሽት ድርጅት ነው። የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ያፈረስ ፤ለባእዳን የሸጠ ፡ፍፁም የክህደት ወንጀል የፈፀመ ድርጅት ነው። አሁን በሚካሄደው በኢትዮጵያ ህዝብ በኦሮሞው ቄሮዎች- በአማራው ፋኖ በጉራጌው ዘርማ በአፋሩ ወጣት በኦጋዴኑ ወጣት በደቡብ ኢትዮጵያ ወጣት ወ.ዘ.ተ. ለአመታት ባካሄደው መራር ትግል መጠነ ሰፊ መስዋእትነት ከፍሎ በፋሽሽቱ ወያኔ ስርአት እየተገደል በእስር እየተሰቃየ ዘግናኝ ቶርቸር እየተፈፀመበት ያመጣው አብዮት ነው።

ከዚሁ መሰረታዊ ጭብጥ ተነስተን በኢትይዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ የለውጥ አብዮት ለማደናቀፍ ወደ 27 ዓመት የጨለማ የግዛት ዘመናቸው በህዝባዊ ማዕበል ተገፍትሮ የተጣለው ወያኔ አልበቃ ብሎት እንደገና ሥልጣንዋ ለመቆናጠጥ ወያኔዎች ለውጡን ለማኮላሸት በመልከ ጥፉ ሤራ በትግራይ ተሰባስበው እየዶሎቱ ይገኛሉ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከባድ መስዋእትነት ከፍለህ ያገኘህው የስርአት የለውጥ ጉዞህ ከወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት የቀን ጅቦች እየተከላከልክ የያዝከው ለመሰረታዊ ለውጣ አብዮት ጉዞህን ቀጥልበት፡ ህዝብ ሃያል በማንም የማይቀለስ ነው።

ከዚህ በፊት የወያኔ ከፍተኛ አመራር የነበሩና አሁንም ያሉ በዚሁ ህዝባዊ አብዮት ተደፍጥጠው መጥፋት አለባቸው ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ ፍላጎት ነው:: ኢትዮጵያና ህዝብዋ ለዚሁ የሲኦል የአገዝ ዘመን ያደረስዋት እነዚህ የወያኔ መሪዎች ናቸው ዛሬ በክቡር ዶ/ር አብይ አሕመድ የሚመራው ያለ የኢትዮጵያ ህዝብ የአብዮት ትግል፤ የፋሽሽቱ ሽብርተኛው ድርጅት ህ.ወ.ሓ.ት. ከግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ለ27 አመታት በህ.ወ.ሓ.ት. የበላይነት ኢትዮጵያን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ኢትዮጵያዊነት አጥፍቶ ክልል በሚል ስም ሰጥቶ፣ ከፋፋይና ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት በህዝቡ መሃከል መለያየት ፈጥሮ መጠራጠር አለመተማን አስፍኖ የኢትዮጵያን ህዝብ፤ ከህዝብ ወደ ህዝቦች የከፋፈለ፣ በቋንቋ በዘር ሃገር በታትኖ ወደ ክልል ብሔርተኝነት ለውጦ፤ የኢትዮጵያዊነት መለያ የሆነው ሰንደቅ ዓላማችን አረንጓዴ ብጫ ቀይ ባንዴራችን ተጥሎ ወደ ክልልዊ ባንዴ የለወጠ፤ ዳር ድንበር የኢትዮጵያ ሉአላዊነት በጀግኖች እናቶቻችን አባቶቻችን ማንም ጠላት ሳይደፍረው ተከብሮ የቆየው የኢትዮጵያ ዳር ድንበር፤ ከየትም የተሰባስበው የህ.ወ.ሓ.ት ባንዳዎች፤ ምኒሊክ የፈጠራት የአማራው ትምክህተኛውና ነፍጠኛው ሃገርንጉስ ምኒሊክ የተፈጠረች ዛሬ ኢትዮጵያ ተብላ የምትጠራ የትምክህተኞች ግዛት.፣ ከዓለም ካርታ ማጥፋትና ማፈረሰ ታሪካዊ ሃላፊነትና ግዴታ አለብን ብለው ፅኑ አቋም በመያዝ ፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት የተነሱት ይህን የወሰኑ በወቅቱ ጊዜ ስሙ ተ.ሓ.ህ.ት. ፤ ከ2 ዓመት በ1971 ዓ.ም.በየካቲት ወር በ1ኛው ጉባኤ ማለት ነው ስሙን ለውጦ( ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ) ህ.ወ.ሓ.ት.መሪዎች

1ኛ አረጋዊ በርሄ

2ኛ ግደይ ዘራፅዮን

3ኛ አባይ ፅሃየ

4ኛ ስብሓት ነጋ

5ኛ ሥዩም መስፍን

6ኛ መለስ ዜናዊ ናቸው።

የህ.ወ.ሓ.ቱ .ማኒፈስቶ አዲስ አበባ በአረጋዊ በርሄና በተባባሪው ግደይ ዘራፅዮን ተዘጋጅቶ የመጣው ከተራ ቁጥር 3 እስከ 6ኛው ተራ ቁጥር ደደቢት በረሃ እንደተሰባሰቡ ስየ አብርሃ አውዓሎም ወልዱን ጨምረው በከፋ መልኩ ፀረ ሃገር ሏላዊነት ፀረ ህዝብ የተስፋፊነት ወረራ አጠናክረው አዘጋጁት። ከዚሁ ተነስተው ከላይ የተጠቀሱ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ለዘመናት ተክብሮ የቆየው የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ማፍረስና ለጊዝያዊ ጥቅም መሽጥ መለወጥ የጀመረው። በበረሃው ቆይታ የወያኔ መሪዎች ይህን ማኒፈስቶ አዘጋጅተው ከጨረሱ ገና ለህዝብ ሳያሰራጩት በ1968 ዓ.ም. ያደረጉት ።

አረጋዊ በርሄና ስብሃት ነጋ ወደ ኤርትራ ሳሕል በረሃ በመጓዝ ከሻዕብያ ድጋፍ ለማግኘት ለሻዕብያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ (ወዲ አፎም) አቅርበው የአቋም ፖሊሳችን ማኒፈስቶ ይህ ነው፡ አውቅና ሰጥታቹህ በአውቅና እንድትቀበሉት ነው ይህን ይዘን የመጣን በማለት አረጋዊ በርሄና ስብሃት ነጋ ተናግረው እንደጨረሱ፤ አድል ስጡን አኔና የሻዕብያ አመራር ጓደኞቼ አንብበት ተነጋግረን ነገ ሁላችን ተሰብስበን መቀበለ እና አለመቀበላችን እናስታውቃለን ተብለው ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፍያ ሄዱ ፤ነገው ደረሰ ተሰበሰቡ ሻዕብያ ተነጋግረው ይዘዉት የመጡ መልስ በኢሳያስ በኩል ሲቀርብ እኛ የሻዕብያ አመራር አሁን የቀረበው የተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.)ማኒፈስቶ ተገቢ በሆነ መንገድ አንብበን ተነጋግረንበታል ስለሆነም፡ ከሃ-ፐ ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ ህዝብ ከፋፋይ ፖሊሲ ሆኖ ስለአገኘነው አንቀበለውም ምክንያቱም ፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት የኢትዮጵያ አንድነት ፍፁም የሚፃረር የህዝቡን ታሪካዊ አንድነት ጸር አፍራሽ ነው፡ ሻዕብያ ይህ አፍራሽ ማኒፈስቶ አይቀበለም እውቅና አይስጥም። ተብለው እያለቀሱ ወደ ትግራይ በረሃ ተመልሰው መጡ።

ለዚሁ ምስክር አያስፈልገዉም ፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነትና ከፋፋይ ፀረ አንድነት ነው። በ1968 ዓ.ም.በየካቲት 5 ቀን በአረጋዊ በርሄ ( የዛሬው ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ) የተዘጋጀው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት (ት.ህ.ነ.አ.ድ. )ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት.) የአቋም መግለጫ ማየቱ በቂ ነው። ይህ የወያኔ የአቋም ፖሊሲ ወያኔዎች በ1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ወረው በቅኝ አገዛዝ ስርአታቸው ከወደቀች በኋላ፤ የኢትዮጵያና ህዝብ ሕገ መንግሥት አድርገው ካለ ኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት በጉልበታቸው የሃገሪቱ ሕግ ሆኖ ባደረሰው እያደረሰ ያለው ጉዳት ሁሉ ኢትዮጵያዊ በራሱ እየደረስ ያለ ሓቅ መነሻው ከዚሁ ነው። ኢትዮጵያ ለመበታተን፤ ሉአላዊነትዋ በመፃረርና ለማፍረስ ሲጠቀሙበት በግልፅ የታየ ሓቅ ነው።

በአማራው እየተፈፀመ የመጣው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከ1969 ዓ.ም. በትንሹ የጀመሩት ወያኔዋች በ1972 ዓ.ም. የአማራው ዘር ማጥፋት በስፋት በማቀጣጠል በሚልዮን የሚቆጠር አማራ ህፃናት እርጉዛን ሽማግሌ ወጣት ሳይሉ ህዝብ አልማሚት በማጥፋት ከትውልድ መሬቱ ያፈናቀለ ይህ የወያኔ ማኒፈስቶ (ፖሊሲ) ነው ፡በዚህም አላበቃም መሬቱ በወያኔ ተነጥቆ ወደ ትግራይ ተካሎ አማራው እንዲበታተን አድርጎታል ለስደትም ለክፉ መከራ የዳረገው ይህ ፖሊሲ ነው ፡በዚሁም አላበቃም አሁንዋ ስአት አማራው ክፉኛ የወያኔ የጥቃት ሰለባ በመሆን በየአካባቢው እየደረሰበት ያለ መጤ እየተባለ በገዛ ሃገሩ ኢትዮጵያ ለመጥፎ ችግርና እንግልት እየተፈጠረበት የሚገኝ ፤አማራው ለዚሁ መከራ የዳረገው ወያኔዎች ሲያዘጋጁት ፖሊስው በፀረ አማራ ወይም ማኒፈስቶ አማራውን ዘሩን ለማጥፋት ከአማራ ትውልድ ቦታው ተፈናቅሎ ተበታትኖ ይከስማል ብለው በጥናት ዘዴ የተዘጋጀ ነው።

የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ቶች. አመራር ፣ አማራ የጠላት ጠላት መራራ ጠላት ነው ብለው መድበው አሰቃቂ ግፍ በዚሁ ኩሩ ኢትዮጵያዊ የፈፀሙበት፡ ተውልድ መሬቱ ተነጥቆ በጉልበት መሳሪያ ውጣ ይህ የትግራይ መሬት ተብሎ ተወሮ ወደ ትግራይ ማካለልም ማለት የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው።ይህ ውሳኒያቸው ተከትሎ በተግባር የፈፀሙት የፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነትና ዳር ድንበር ፤ለጊዚያዊ ጥቅማቸው ፤ሲሉ የህ.ወ.ሓ.ት.መሪዎች በአረጋዊ በርሄ የሚመራ የማፍያ ናዚ ድርጅት የፈፀመው አብነት ላቅርብ፡ ፡ 1ኛ ሁሉ ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ሓቅ ነው ።

በ1969 ዓ.ም. በኤርትራ ውስጥ ሁለት ድርጅቶች ኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል አለባት ፤ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም፤ የሚሉ ነበሩ ፤በዘመናዊ ትጥቅ የተደራጁ ናቸው ፤እነዚህም //
1ኛው ጀብሃ (ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ )

2ኛው ሻዕብያ (ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ/ ህ.ወ.ሓ.ት. ደደቢት ውስጥ ቢሾጎጥም በትጥቅ በኩል እጅጉ የተራቆተ ድሃ፤ በኢኮኖሚ ሁኔታውም ድሃ ነበር ሆነም ቀረም በሻዕብያ በኩል ከሚደረግለት ድጋፍ በቀር ራሱ የቻለ ድርጅት አልነበረም ።ህ.ወ.ሓ.ት. ግን ደደቢት በረሃ ሲወርድ ሰንቆት የመጣ ትልቅ መሳሪያ ነበረው- እነዚህም – ውሽት-ማጭበርበር- አስመሳይነት -ከሃዲነት -ፀረ ኢትዮጵያነት -ፀረ ህዝብ -ከፋፋይ – ዘረኝነት -አውራጃዊ ጎጠኝነት =የተቀነባበር ሽብርተኛነት – ቂም በቀል-ተንኮል ወ.ዘ.ተ።

ህ.ወ.ሓ.ት. ለትግራይ ህዝብ ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ ጥቃቱን በመሰንዘር በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሽማግሌዎች ወንድ ሴት ወጣት ሴቶች ወንዶች ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ብዙ ሓለዋ ወያኔ እያስገባ በሶቆቃ ቶርቸር ፤በጅምላ ጉድጓድ እያስገባ የትግራን ህዝብ የፈጀ ፤ በጥይት ደብድቦ በመረሸን በመግደል ፀረ ትግራይ ድርጅት ሁኖ ያደገው።

ይህ ድርጅት በምንም መልኩ ለትግራይ ህዝብ ያልቆመ ከትግራይ ህዝብ ድጋፍ ያልተሰጠው ጥቂት ቁጥር ያላቸው ማፍያና የባንዳ ልጆች የተመሰረት ራሱ የትግራይ ህዝብ ስም ካባ ለብሶ የተፈጠ በፀረ ኢትዮጵያ ባእዳን ሃይሎች የቆመ ድርጅት ህ.ወ.ሓ.ት. ነው።በትግራይ ህዝብ ይቅር በማይባልበት ርህራሄ በሌለው ለትግራይ ህዝብ አጥቅቶታል። የትግራይ ድርጅት አለመሆኑም የወያኔ መሪዎች ያውቁታል ፤ አረጋዊ በርሄ ጠንቅቀው ያውቃል እነ ግደይ ዘርአፅዮ ፤ስብሃት ነጋ ወ.ዘ.ተ.የባንዳ ልጆችም ያውቃሉ ።ደደቢት በረሃ እንደገቡም በ1968 ዓ.ም. የካቲት ወር የተዘረጋው የህ.ወ.ሓ.ት፣ ማኒፈስቶ (የአቋም ፖሊሲ) በአረጋዊ በርሄ ዋና አዘጋጅነት የተዘጋጀ መሆኑ ሳረጋግጥ ፤የዘር ማጥፋት በአማራው ፣የትግራይ ህዝብ ግድያ እኔ የለሁበትም ብሎ ደጋግሞ ስለሚክድ ፤ይህ ማኒፈስቶ ሲዘጋጅ አላውቅም ብሎ ስለካደ በሕግ ስለ ሚጠየቅበት የኔ አይደለም ብሎ እንዳይክድም ቁልጭ ብሎ የሚታየው የራሱ የእጅ ፅሁፉ በዘረጉት የፖሊሲ አቋም በግልፅ ይታያል። ሃገርና ህዝብ ያወደመ ለዚህ ሁሉ ኢትዮጵያና ህዝብዋ የዳረገ ይህ የአረጋዊ በርሄ የአቋም ፖሊስ ነው።

አሁን የወያኔ ፋሽሽት ስርአት የሚጠቅምበ ፤የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ሆኖ 100 ሚልዮን ህዝብ የሚገዛ ያለ ይህ ማኒፈስቶ ነው። ይህ ማኒፈስቶ ሆን ተብሎ በጥናት የተዘጋጀው 1ኛ የመስፋፋት ፖሊሲ ያቀፈ የህዝብ ማንነት የነጠቀ የገፈፈ ፀረ ህዝብ ሰሜን ጎንደር ሙሉን ያካተተ ወልቃይት -ጠገዴ -ጠለምት ቃፍታ ሁመር በወሎ በኩል ከሃሸንጌ አንስቶ እስከ ራያና ቆቦ የወረረ 2ኛ አማራ ደመኛ ጠላት ብሎ ዘሩን እስከ ማጥፋት የደነገገ ፖሊሲ በተግባርም የዋለ 3ኛ ፀረ ኢትዮጵያ አንድነትና ሏአላዊነት ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ ከፋፋይ በታኝ ህዝብን ወደ ደም መፋሰሰ የሚያስገባ ብጥብጥና በማጋጨት እልቂት ፈጥሮ ኢትይጵያ ለመበታተን ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነው 4ኛ ህ.ወ.ሓ.ት. ፀረ ሃይማኖት አቋም ይዞ የተፈጠረው ገና ከመጀመሪያ ትግሉ ነው፤ ይህ ፖሊሲም በተግባር እንቅስቃሴው የጀመረው ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን፤በዚህ መሰረትም ድርጅቱ ፀረ እስልምና ሃይማኖትና ክርስትና ሃይማኖቶች ሙሉ በሙሉ የሚያወግዝ ነወ፤ ፖሊሲው በዋና መሪነቱ ያዘጋጀው የሰነደው አረጋዊ በርሄ ተግባራዊ እርምጃም መውሰድ ቀጠለ።

በዚሁ ማኒፈስቶ ማዘጋጀት ተባባሪ የነበሩት ግደይ ዘራፅዮን መለስ ዜናዊ ስብህት ነጋ አባይ ፀሃየ ስዩም መስፍን ስየ አብርሃ አውአሎም ወልዱ በዋናነት እየተረዳ ሲዘጋጀ ፤ቄሶቹም የቅስና ቆባቸው እንዲጥሉ ማዋከብ የተጀመረበት በዚህ ወቅትም ነበር ። የቅዱስ ነዋያት ዝርፍያም አብሮ ቀጠለ ብዙ ቤተክርስትያናትም ተዘርፈዋል ።በእምነታቸው የፀኑ ቀሳውስትም ተገድለዋል።

ወደ ዋናው ሃሳቤ ስመለስ ፡ባድመን በተመለከተ በ18/06/2018 ዓ.ም. በሜድያ ድህረ ገፆች ባድመ ብቻ ሳይሆ ብዙ ቦታዎች ያቀፈ ሰፊ የኢትዮጵያ በትግራይ ጠ/ግዛት ሲተዳደር የነበረው እንዴትብሎ ለኤርትራ ተላልፎ እንደተሰጠ እውነታው (የባድመ ነገር )በሚል አርእሰት ዝርዝር ሁኔታውን በመግለፅ ለኢትዮጵያ ህዝብ አቅርቤው አለሁ እውነተኛ ሓቁን አስቀምጨው አለሁ።

በዚሁ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ ሜድያ ድረ ገፆች- ዘሃበሻ -ሳተናው -አባይ ሜድያ -ኢትዮ-ሜድያ -ኢትዮጵያ ነገ – ኢ.ሜ.ፍ EMF(ethiopian media forum)- ቋጠሮ (Qautero)- ጎልጉል- ወልቃይት ድረ ገፅ – ሁላቹህ ለምታደርጉልኝ ሙሉ ያልተቆጠበ ድጋፍና ትብብር እያመሰገንኩ ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለምትሰሩት መልካም ሃገራዊ ተግባር ውለታቹህ ይክፈላቹህ ።

በ1969 ዓ.ም. ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በነበረው ከባድ ችግር ፤ የመሣሪያ ትጥቅ ፤ ገንዘብ ፤ሌላም በችግር ማእበል ውስጥ ስለነበር አማራጭ ሆኖ ያገኘው ኤርትራ ውስጥ የሚገኙ በትጥቅ ትግል የተሰማሩ በትግራይ ለኤርትራ አዋሳኝ የሆኑ ወረዳዎች ለመሸጥ በ1969ዓ.ም. እቅድ በማውጣት ወዲያውኑ ወደ ተግባር በመለወጥ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ጥቅም ለማግኘት ብለው ከባድመ እስከ ዓዲ ፀፀር ሸላሎን ጨምረው ዓዲ አውአላ ዓዲ ሃገራይ ዓዲ ነብርኢድ ዓዲ ዳዕሮ ሰመማ ጭላ ፤እገላ ወረዳ አጋሜ አውራጃ ውስጥም ዛላምበሳ- ኢሮብ (ዓዲ ወልዱ ዓዲ ስባጋድስ )- ዓሊተና- ባዳ ትግራይ – የአፋር መሬቶች ብዙ ወ.ዘ.ተ. የኤርትራ ቦታዎች (መሬት )ነው በማለት በ1972 ዓ.ም. ህዳር ወር በአባይ ፀሃየ፣ በመለስ ዜናዊ፣በወያኔ መሪዎች በአረጋዊ በርሄ፣ በግደይ ዘራፅዮን፣ በስብሃት ነጋና በስዩም መስፍን ተመርጠው ተወክለው እገላ ዓዲ ጨጓር ቁሸት እገላ ወረዳ ዓድዋ ወረዳ ውስጥ ፤ከፆሮና ኤርትራ የአንድ ሰአት ተኩል ርቀት የምትገኝ ቦታ ሆነው የኤርትራ መሬት ነው ሻዕብያ ያነሳው የመሬት ጥያቄ ትክክል በመሆኑ የኢርትራ መሬት በመሆኑ ስላመንበት አስረክበናል ብለው ተፈራርመው ለሻዕብያ ለኤርትራ አስረከቡ -ሰጡ- ሸጡት፤ ለግዚያዊ ጥቅም ብለው። በዚህ አካባቢ የተፈጠረው ችግር ያለቀው የሰው ሂወት የወደመው የሃገር ንብረት የኢትዮጵያ ህዝብ በስፋትና በጥልቀት ስለምታውቀው ልተወው ይህን ሁሉ ችግር የፈጠሩት ተጠያቂው የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ነው፤ ከላይ በተጠቀሱ አመራሮች ህዝብና መሬቱ የሸጡት ናቸው፤ ለተፈጠረው ችግርም ተጠያቂ የሚሆኑት የህ.ወ.ሓ.ት.መሪዎች እንጂ ሌላ የለም፤ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር በተፈጠረው ጦርነት የሰው እልቂት የንብረት ውድመት ለሃያ ዓመታት ለተፈጠረው ችግር ያመጡት የፈጠሩት በአረጋዊ በርሄ የሚመራ የህ.ወ.ሓ.ት. የአመራር ቡድን፥ ግደይ ዘራፅዮን፣ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ ፣አባይ ፅሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለጊዚያዊ ጥቅም መሬትና ህዝብ ሽጠው ያመጡት መዘዝና ችግር ነው። የወያኔ ጥፋት እንጂ ሻዕብያ በዚሁ በኩል ይህ ሚና ነበረው ተብሎ ለመናገር አትችልም ሃቁን ለመናገር ለዚሁ ወንጀል ዋናው ተጠይያቂው ግንባር ቀደሙ የህ.ወ.ሓ.ት. ስድስቱ አመራር ናቸው ።
ህ.ወ.ሓ.ቶች ዛሬስ ምን እያሉ ናቸው ? በትግርኛ አንድ ተረት አለ “ዘበንያ ግርምቢጥስ ማይ ንዓቀብ፟ ይፈሥስ” በአማርኛ -ደግሞ ዘመነ ተገላብጦሽ ውሃ ወደ ሽቅብ (ይፈሳል)ማለት ሲሆን በሃገራች ኢትዮጵያ ህዝብ አስደማሚ ነገር በሚያይበት ወይም በሚሰማበት ይህን ተረት ይጠቀማል::

አሁንም በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለው በፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነትና አንድነት በፀረ ህዝብ እንድነት ኢትዮጵያና ህዝብዋ በታትነው ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ምኒሊክ አማራውን አደራጅቶ የፈጠራት ሃገር ፈርሳ ከዓለም ካርታ እንድትጠፋ እናደርጋት አለን ብሎ ደደቢት በረሃ የወረደው በአረጋዊ በርሄ የሚመራ ድርጅት ማ.ገ.ብ.ት. ደደቢት በረሃ እንደገባ ተ.ሓ.ህ.ት. ህ.ወ.ሓ.ት. ትልቁ እስትራተጂካዊ ፖሊሱም ትግራይ ከኢትዮጵያ ገንጥሎ መሬት ወሮ ታላቅዋ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ትግራይ ለመመስረት አላማውና ዋና አቅዱ እስከ 1982 ዓ.ም. በኋላም መንገዱ ስለቀናቸው ኢትዮጵያ በወራሪነት ኢትዮጵያ ተቆጣጠሩ ፣በቅኝ ገዥነት። ወያኔ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ለዲሞክራሲ ብሎ ደደቢት በረሃ አልወረደም። ትግራይ ለመገንጠል ካልሆነ በስተቀር ።

ህ.ወ.ሓ.ት. በረሃ ወርዶ 17 ዓመታት የታገለው ትግራይ አስገንጥሎ የትግራይ መንግሥት ለመመስረት እንጂ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ዲሞክራሲ ብሎ አልታገለም አንድም የሰው ሂወት አልከፈለም ፍፁም ውሸት ነው ።ለማስመሰል የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች በህዝብ ፊት የውሸት ፕሮፓጋንዳቸው ይናገራሉ አውነት መስሎት የሚያደንቃቸው ጥቂት ሰው ሊገኝ ይኖራል፤ አብዝሃ ኢትዮጵያዊ ግን አይቀበላቸውም ፤ እነዚህ እሥስቶች ህዝብን ለማደናገር የሚጠቀሙበት ስልታቸው ነው የማታለልና አጭበርብሮ ውሸት ከማስመሰል አቀነባብረው ማደናገር ልምድ የተካነው የድርጅቱ ዋና መሪ የነበረ በ1980 ዓ.ም. ከድርጅቱ በስልጣን ሽኩቻ ሲሰናበት $35000ሺህ ጉርሻ ተቀብሎ ሂድ ብለው የሸኙት አረጋዊ ብርሄ ።

የኢሳት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ፕሮግራሙ ማን አዘጋጀው ብሎ ሲጠይቀው ፕሮግራሙ ተደብቀው ያዘጋጁት የፃፉት እነሱ ናቸው እኔ አላውቀውም ? እውነታው ግን እሱ ነው ሙሉ በሙሉ ያዘጋጀው የራሱ የእጅ ፅሁፍ ነው ሌላው ተጨማሪ በእንግሊዝኛ The Origins Of The Tigray People’s Liberation Front .African Affairs (2004) በሚል ኧርእስት በፃፈው ኢትዮጵያና አማራን የሚዘልፍ አስነዋሪ ፅሁፍ ፅፎ ማሰራጨቱ ምንኛ በኢትዮጵያም ሆነ በአማራው የመረረ ጥላቻ እንዳለው ያሳየበት ሰነድ ነው ካወጣው የወያኔ ፕሮግራምም የተያያዘ መሆኑ ለማረጋገጥ ያስችላል ይህ ፅሁፍም ህዝብ ይመልከተው ። ሌላኛው ክህደቱ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት የሚለው እንሱ ናቸው ሸንቅረው ያስገቡት በኢሳት ቃለ መጠይቅ የተናገረው ውሸት የፃፈው ራሱ ነው፤ ኤርትራን ለማገንጠል በህ.ወ.ሓ.ት. የነበሩ አመራር ሁሉ የታገሉለት አረጋዊ በርሄ የተለየ አቋም አልነበረውም ለዚሁ ግንባር ቀደም የነበረ መሪ ነው ።

በሌላ በዚሁ 2018 ዋሽንግቶን የኢትዮጵያውያን ሬድዮ የሰሙት የጠየቁኝ አረጋዊ በርሄ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ስል ትግሉ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የሃገራችን ሏላዊነት አይደፈርም ብየ በፅናት በሞቆሜ ብዙ ችግር የደረሰብኝ እኔ ነው የማውቀው ብሎ ተናገረ እውነት ነው ወይ ?ብለው ሲጠይቁኝ ፤ውሸቱ ነው፤ የሚል መልስ ሰጠኋቸው ፤ደግሞም ልክ ነው። ያላደረከው አድርጌው ነበር ማለት መጥፎ ውሸት ከመሆኑ በላይ ማንነትህም ለሰው ትእዝብት ይዳርገሃል።

በተለያዩ ፓልቶክም ይናገራ በውሸት ርካሽ የዘገጠ ተቀባይነት ለማግኘት ፤ይህ ግን ተመልሶ ራሱን ያጋልጠዋል ፤ከፈፀምከው ወንጀል አያድነውም፤ እኔ ከተ.ሓ.ህ.ት.ጀምሮ እስከ ህ.ወ.ሓ.ት›እስከ በነበርኩበት ጊዜ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሏአላዊነት ስል ብዙ ችግርና ተቃውሞ ይፈጠርብኝ ነበር በማለት እየተናገረ ያለው፤ ፍፁም ደረቅ ውሸት ነው ማን ነበር ፀረ ኢትዮጵያ ሏአላዊነት ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ራሱ አረጋዊ በርሄ ነው።እኔ ይህ ፅሁፍ አቅራቢ ወያኔን የተቀላቀልኩት ገና ደደቢት በረሃ ሳይወጣ ማ.ገ.ብ.ት.እንደተመሰረተ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ነው በረሃም ወደ ትግሉ የተቀላቀልኩት በ10ወር ዕድሜው ነው ስለዚህ በከተማ ብንተዋወቅም የበረሃው ተግባሩና የፈፀማቸው ጉዶች በሚገባ አውቃለሁ ስለዚህ እኔ አረጋዊ ብርሄ የማውቀው ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ደግም የትግራይ ህዝብ ያጠፋ የጨፈጨፈ የገደለ የአማራ ዘር ያጠፋ ኢትዮጵያ አሁን ለወደቀችበት ችግር መከራ ያበቃት አረጋዊ በርሄ ነው ፡ለዚህም ቁጥር አንድ ተጠያቂ አረጋዊ ነው ራሱ ያዘጋጀውን ፕሮግራም እኮ ያጋልጠዋል ።

ስለ ባድመ እየተናገርው ያለ የሻዕብያ መንግሥት ትግራይን ወሮ የወሰደው መሬት በአልጀርስ ፍርድ የተሰጠኝ የሚለው በኢትዮጵያ አዲሱ ጠ/ሚኒስተር የአልጀርሱ ፍርድ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ለኤርትራ መስጠት አለብን ብለው ሊሰጡት ስልሆነ ይህም ፀረ ትግራይ ህዝብ ስለሆነ የት.ዴ.ት(TAND) ማእከላይ ተሰብስቦ የጠ/ሚኒስትሩ ሃሳብ አንቀበለውም እኛም በተሎ ስለምንገባ ይህ በዛሬው መንግሥት የተላለፈው በመቃወም ለኤርትራ እንዳይሰጥ እናቆመው አለ፡ ድርጊቱም እናወግዛለን ህዝብ ያልተወያየበት በጓሮ ተደብቀህ የሚፈፀም ነገር የለም የትግራይ ህዝብም ለተቃውሞ እንቀሰቅሳለን ግደይ ዘራፅዮ አስከትሎ ኢትዮጵያ የገባው።

በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን -ትግራይና ህዝብዋ ለኤርትራ ሸጡን ይላል ።ራሱ የህ.ወ.ሓ.ት. ቁንጮ መሪ በነበረበት ጊዝያዊ ጥቅምን ለማግበስበስ ሲል አሳልፎ ሰውና መሬቱ የሸጠው ፤ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ አይደለም ። ሰውና መሬት አዳምሮ የሸጠ አረጋዊ በርሄና አምስቱ የወያኔ ከፍተኛ መሪዎቹ ናቸው ፤ ዛሬ ተቆርቋሪ መስሎ አዲስ ባርኖስ አጥልቆ ሰው አያውቀኝም ብሎ ማሰብ ተጨማሪ ውርዴት ነው። እነሱስ ይህ በኢትዮ-ኤርትራ ሰፊ የትግራይ ግዛት አሳልፈው ሲሸጡ ለአካባቢው ህዝብ አማክረዋል? አላደረጉም በሚስጥር ነበር የፈፀሙት ።ሌላው ይህን አጋጣሚ ሊጠቀሙበት የፈለጉ በትግራይ ህዝብ እነ አረጋዊ በርሄ ርህራሄ በሌለበት Barbaric በሆነ አካሄድ የትግራይ ህዝብ በገጠር በከተማ አጥቅተዋል ገድለዉታል ያለው ሃብቱ ንብረቱ ውርስ ለድርጅታችን እየተባለ ብዙ ግፍ ፈፅመውበታል በትግራይ ህዝብ የፈፀሙት ከባድ ወንጀል ለመሸፈን ይጠቅመናል ብለው ያሰቡት የማጭበርበ ዘዴም ነው።

ውድ የትግራይ ህዝብ ሆይ !! የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ከ1968ዓ.ም. አንስቶ ባንተ ላይ የፈፀሙት ግፍና የሰቆቃ ግድያ አንተ ራስህ በግልፅ የምታውቀው ስለሆነ ራስህ ትመሰክረዋለህ በወያኔዎች ተገድለሃል ሃብት ንብረትህ ተዘርፈሃል ፡የወለድካቸው ልጆችህ ተነጥቀ ወደ ትግል በረሃ አውርደው ይረዱኛል ብለህ ያሳደካቸው ልጆችህ በወያኔ እየተገደዱ በረሃ ወርደው ታጋይ ተብለው በየበረሃው ወድቀው ቀርተዋል ፡እነዚህ ልጆችህ የቀይ ኮከብ ዘመቻ በ1974 ዓ.ም ኤርትራውስጥ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሻዕብያ በሚካሄደው ጦርነት ከ160000 ሺህ በላይ የትግራይ ወጣት ወንድ ሴት ተልከው ኤርትራ ሳሕል በረሃ ገብተው በተካሄደው ከባድ አውዳሚ ጦርነት ሞተው ሳሕል በረሃ ቀርተዋል፡ ይህም መስካሪ አያስፈልገውም የትግራይ ህዝብ ራስህ የምታውቀውሓቅ ስለሆነ ከነዚህ ውስጥ አካለ ጎደሎ ሆነው በሂወት የተመለስ 1347 ብቻ ናቸው።

ለዚሁ የጥፋት ድርጊት ተጠያቂዎች የህ.ወ.ሓ.ቱ. ቁንጮ መሪዎች አረጋዊ በርሄ ግደይ ዘራፅዮን ስብሃት ነጋ መለስ ዜናዊ አባይ ፀሃየ ሥዩም መስፍን ናቸው ።
ወድ የትግራይ ህዝብ ሆይ !! የህ.ወ.ሓ.ት. አመራሮች ትግሉ ከተጀመረበት ከ1967 ዓ.ም. አንስቶ አንተን እየገደሉን እያጠፉ ልጆችህን ከየቦታው በሃይል እያስገደዱ ትግሉን ተቀላቀሉ በማለት በማስገደድ ሳይወድ በግድ በሃይል ወደ ትግል ሜዳው በማስገባት ዛሬ በየትም ቦታ ወድቀው ቀርተዋል አጥንታቸው አይገኝም ፣ይብላኝ ካለ ዕድሜው የትም ሙቶ ለቀረው የትግራይ ወጣት ወንድ ሴት አንጂ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች እማ ተንበሽብሽው የተንደላቀቁ ቱጃር ሃታሞች ሚልየኖሮች-ቢሌኖሮች ሆኖዋል። በሰው ልጅ ሂወት ሸቅጠው። በዚህ የወንጀል ድርጊታቸው ሳያበቁ በአንተ ስም እየሸቀጡ ባንተ ስም እየነገዱ፤ ከመጡ እንሆ እስከ ዛሬ ድረስ 43 ዓመታት አስቆጥረዋል።

ኢትዮጵያን በወያኔ ቅኝ አገዛዝ በምትወድቅበት ጊዜ በሁሉ የሃገሪቱ ሃብት በስብሃት ነጋ -በአርከበ ዕቁባይ- በአባይ ፀሃየ- በፃድቃን ገብረተንሳይ- በስየ አብርሃ- ወ.ዘ.ተ.የፖሊት ቢሮ አመራሮች የሚመራ ቡድን ተደራጅቶ የኢትዮጵያ ሃብት ንብረት የህዝብ ገንዘብ-የሃገሪቱ ተቀማጭ ወርቅ-ታሪካዊ መፃህፍት- ታሪካዊ ሰነዶች በስፋት ተዘርፎዋል ። ባንኮች፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ -የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ- የመንግስት ካዝናዎች- ሌሎች የመንግሥት የገንዘብ ተቋማት ሁሉ ሙልጭ አድርጎ የዘረፈው ህ.ወ.ሓ.ት. ነው ።ይህ የተዘረፈው ገንዘብና ወርቅ ኢፈርት (ት.እ.ም.ት.) የሚባል ግዙፍ ድርጅት አቋቋሙበት።

እኔ ትግራይ ጠ/ግዛት ተወልጄ ያደጉ ኢትዮጵያዊ ነኝ ኩሩ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ቁምነገረኛ ህዝብ አምርሮ የሚያወግዘው የሚጠላው ዝርፍያ ስርቆት ውሸት ነው ። ታድያስ ወያኔዎች በ1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በሚቆጣጠሩበት ወቅት የዘረፋት የሃገር ሃብት ግዙፍ ኢ.ፈ.ር.ት.ወይም ት.እ.ም.ት. ድርጅት አቋቁመው ሌብነታቸው ለመሸፈን ፤ይህ የህ.ወ.ሓ.ት.አይደለም ኢ.ፈ.ር.ት.አንጡራ የትግራይ ህዝብ ሃብት ንብረት ነው እያሉ ባንተ የትግራይ ህዝብ እየሸቀጡ በስምህ እየነገዱ ናቸው ።ህ.ወ.ሓ.ት. ደደቢት በረሃ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ አንተን እየገደለ ያፈራሃው ንብረት ሃብት እየወረሰ በሌላ መንገድ ደግሞ ባንተ ስም እየማለ ለመጥፎ አደጋ እያጋለጠህ እስከ አሁን ቀጥሎበታል ፤አንድ ምሳሌ ልስጥ፤ በ1977 ዓ.ም. የተከሰተው ድርቅ ባንተ የትግራይ የደረሰብህ ችግር፤ ሞት-ርሃብ-በሽታ- ያፈራሃቸው የቤት እንስሣት በሞት አልቀው የትናንትናው ክስተት ነው ፤የትግራይ ህዝብ እንደ ቅጠል የረገፈበት ሞቶ ቀባሪ ያጣበት የቤት እንስሣት ያለቁበት ወንዞች ኩሬዎች የደረቁበት እጅግ ክፉ ዓመት ነበር ፤ ባንተ ስም ተለምኖ የዓለም ህዝብ አቤት ብሎ ያለቀሰበት ፤ ዓለም በሙሉ እጁን ዘርግቶ የላከው ነብስ አድን ምግብ አልባሳት የተለያዩ የቤት ቁሳቁስ የእርሻ መሳሪያዎች ጥሬ ገንዘብ በብዙ መቶ ሺህ ሚልዮን የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላር የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች በመለስ ዜናዊ በስብሃት ነጋ የሚምራ ፖሊት ቢሮ (ሥራ አስፈፃሚ ) ተባብሮ የመጣው እህል የምግብ ቅባት የህፃናታ አልሚ ምግብ አልባሳት ሁሉ ለትግራይ ህዝብ የመጣ እርዳታ ሱዳን ውስጥ ፖርት ሱዳን ያጣበበው ከመርከብ ወደ መርከብ እየተሸጋገረ ለአረቦች ግብፅ፤ሶሪያ፤ኢራቅ ፤ኢራን ፤ሱዳን ፤ሊብያ ፤ሊባኖስ ቤሩት ፤ወ.ዘ.ተ.የህ.ወ.ሓ.ት. እንዳለ ገበያ አውርደው ሸጠው ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉት እንተ የትግራይ ኩሩ ኢትዮጵያዊ በየትም ወድቀህ ቀባሪ በማጣትህ ልጆችህ ባለቤትህ ራስህ የጅብ ቀለብ ሁነህ ቀርተሃል የመጣው በብዙ መቶ ሺህ ሚልዮን የአሜሪካ ዶላርም በህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ካዝና ገባ ።

ይህ ባጭሩ የገልፅኩት የፈፀሙት የወንጀል ወንጀል ሳይበቃቸው አሁንም ባንተ ስም እየነገዱብህ ይገኛሉ ።ውድ የትግራይ ህዝብ ይህ ብቻ አይደለም ወያኔዎች አንተ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ከወገንህ ኢትዮጵያዊ እንድትራራቅ ብዙ የተንኮል ሴራ ባንተ ስም ስርተዋል አካሂደዋል ከአማራ ከኦሮሞ ከጋምቤላው ከአፋሩ ወ.ዘ.ተ.ባልዋልከው ባልፈፀምከው ወያኔዎች በሰሩት ድርጊት ባንተ ስም እያሳበቡ ከብዙ ኢትዮጵያ ወገንህ ችግር እየፈጠሩብህ ይገኛሉ አሁንም አንድ ባንተ ስም የተደረገው ልነግርህ እፈልጋለሁ አንድ የዓድዋ ልጅ የሆነው ዶ/ር አለምሰገድ አሳየኽኝ የተባለው መለስ ዜናዊ እያለ የጥናት ፅሁፍ ብሎ ባሳተመው አዲስ አበባ ውስጥ የትግራይ ህዝብ 85%የአማራ ህዝብ እጅግ ይጠላል ለምን እንደሚጠላውም ይዘረዝራል ይህ ግን በወያኔ ህ.ወ.ሓ.ቶች የተፈተለ የትግራይ ህዝብና የአማራ ህዝብ ለመለያየት ለማጣላት ሆን ብለው ያወጡት እደገኛ ዘዴ ነው ፡አንተ የትግራይ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ከወገንህ ኢትዮጵያዊ አማራ ለማጣላትና የችግር መፍጠሪያ ዘድያቸው ነው አንተ ባልተናገርከው በማታምንበት የትግራይ ህዝብ እንዲህ አለ ብለው በመፅሃፍ ማሳተማቸው ምንኛ ህ.ወ.ሓ.ት. ክፉ ጠላት በጀርባህ እንዳለ ልታውቀው ይገባል ፡፡እዚህ ላይ የሚነሳ ጥያቄ ወያኔ ይህ ለክፉ አደጋ የሚዳርግ ለምን በትግራይ ህዝብ ሆነ? ፀሃፊው ዶ/ር አለምሰገድ አሳየኝ በወንጀል እንደሚጠየቅበትስ ያውቃል ?ጊዜው ሲመጣ የትግራይ የሚያነሳው በመሆኑ በመተማመን ልቆይ ።ሌላ አብነት ላቀርብ እፈልጋለሁ በመለስ ዜናዊ ወቅት የህ.ወ.ሓ፣ት፣ ካድሬዎች መላው የአዲስ አበባ ክልል በ5 ለአንድ ህዝቡ ተጠርንፎ ሲሰቃይ ከነዚህ ካድሬዎች ውስጥ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአቢሄርና(ሞንጀርኖ) ተስፋማሪያም( ዜር ፎር) የሚባሉ ሲሆኑ ሁለቱም የወያኔ ነባር አባሎች ናቸው የአንድ ቀጠና ሃላፊዎችም ነበሩ ፈትለወርቅ ማለት የቀኛ/ ገብረእግዚአቢሄር ልጅ ዓዲአብዮቶ ናት፣ በየስብሰባው የምትናገረው የትግራይ ህዝብ አማራን አይወድም አማራ ይጠላል እያለች ስትሰብክ የቆየች አሁን የትግራይ መሪ ባለስልጣን ናት ከመለስ ዜናዊ የተሰጣት ህዝብ ከህዝብ የማጋጨት ፖሊሲ ስታራምድ እንደነበረች ትግሬው አማራው የሚያውቀው ሓቅ ነው ።ብዙ ማቅረብ ይቻላል ግን በዚሁ ላቆም ።

መፍትሄው የትግራይ ህዝብ ሆይ!! ህ.ወ.ሓ.ት.በጀርባህ እንድ መዥገር ተጣብቆ ያለው አስቸጋሪ ፋሽሽት ሽብርተኛ ቡድን መላቀቅ አለብህ ተላቀህ ከኢትዮጳያ ህዝብ ወገንህ ተደምረህ ወደ ለውጥ አብዮቱ ተቀላቀል፤ ይህ ዘረኛ የወያኔ ቡድን ነቅለህ ጣለው እንተን እንደምሽግ እየተጠቀመ ብዙ ችግር እየፈጠረብህ ከወገንህ የኢትዮጵያ ህዝብ ቅራኔ እየፈጠረብህ ነው፡ መላ በል ባንተ ስም እየተነገደ ነው ፡ወያኔዎች ሲሸጡህ ሲለውጡህ ነው የሚውሉት ያሉ ባነተ ስም እየነገዱ እየተጫወቱብህ ነው ያሉት ፡ይበቃሃል 43 ዓመት ሙሉ ቀጥቅጠው አሰቃይተው በባርነት በጨለማ ስርአታቸው አንተን በማዋከብ የፈረስ ቤትህ ታውቀዋለህ አምስት ለአንድ ጥርናፈ ማለት የባሪያ ስርአት አገዛዝ ነው ፡በገዛ ሃገርህ ኢትዮጵያ በባርነት በጥቂት የወያኔ ሽብርተኛ ጉጅሌ ስምህ እንዴት መጠቀሚያ ይሆናል፡ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ በዶ/ር አብይ አህመድ የሚምራው የህዝብ አብዮት ወደ ፊት እየተራመድ ብዙ ለውጥ እየመጣ ባለበት አማራው ኦሮሞው ወ.ዘ.ተ. የአዲሱ ለውጥ ተቋዳሽ በመሆን ነፃነታቸው እያጣጣሙት ለሙሉ ነፃነት ወደ ፊት እየገፉ ይገኛሉ አንተ የትግራይ ህዝብ ግን በህ.ወ.ሓ.ት. የቀን ጅቦች አሁንም ታፍነህ ትገኛለህ መላ በል የኢትዮጵያ ህዝብ ክጎንህ ነው ያለ ።የትግራይ ህዝብ ሆይ ፣ወያኔ ሲፈጠር ከመነሻውም ትግራይን ለማስገንጠል ፀረ ኢትዮጵያ መሆኑ ካንተና ከአማራ ህዝብ በበለጠ የሚያውቀው የለም ፡የትግራይ ህዝብ የደደቢት አይጥ ድርጅት ህ.ወ.ሓ.ት. አይቀበልም ብለህ አሽቀንጥረህ የጣልከው በ1968ዓ.ም አንተ የትግራይ ህዝብ ነህ።

ለዚህም ከባድ መስዋእትነት ከፍለህበታ የወያኔ መሪዎች በጊዜው የነበሩ አመራር ዋናው መሪ 1ኛ አረጋዊ በርሄ 2ኛ ግደይ ዘራፅዮን 3ኛ ስብሃት ነጋ 4ኛ አባይ ፀሃየ 5ኛ ሥዩም መስፍን 6ኛ መለስ ዜናዊ ሆነው የእነዚህ ተባባሪ የነበሩም ስየ አብርሃ ፤ አዋዓሎም ወልዱ ።በየካቲት ወር 1968 ዓ.ም. በአረጋዊ ብርሄ የተዘጋጀ የህ.ወ.ሓ.ት. የአቋም ፖሊሲ ለህዝብ ሲበተን በመጀመሪያ የተቃወምከው እንተ ነህ ከቦታው ሰብስበህ የጠባቦች ፀረ ኢትዮጵያ የደደቢት አይጥ መፅሃፍ ብለህ በእሳት ያቃጠልከው አንተ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነህ ፤ለዚሁም ከባድ መስዋእትነት ከፍለሃል ተገድለሃል ንብረትህ ሁሉ በህ.ወ.ሓ.ት. ተወርሰሃል በትግራይ ከተሞች በአርጋዊ በርሄ የሚመራ ድርጅት የፈፀመው ግድያ የፈሰሰው ንፁህ ደም በአይን ቢለንህ አይተሃል ከመቀሌ እነ አብርሃ ፓትሪስ፣ ከሁልት ዓውላእሎ እነ 10 አለቃ ገብረስላሴ -ባቡ ዘገየ ከአባቱ ደጃዝማች ዘገየ ከአዲግራት እነ ደጀን፣ከዓድዋ እነ አቶ ቢተው በርሃኔ፣ ከአክሱም እነ መምህር መላኩ መንገሻ ከሽሬ እንዳሥላሴ እነ ተከስተ አስፍሃ፣ ከተምቤን እነ አርአያ ለአብነት ከየአውራጃው ያነሳሁት አንዳንድ ሰው ባነሳ የተገደሉት ግን ከ600—800 የሚደርስ ነው ።

ወያኔዎች ፈዳያን ብለው የሰየሙት አጥፍቶ ጠፊ ገዳይ ሽብርተኛ ቡድን ፤ሲፈፅሙት የነበረው ግድያ አይተኍዋል ግድያ የሚፈፀሙት የቀን ሽብር ነበር ህ.ወ.ሓ.ት.ከ1970 ዓ.ም. መስከረም ወር ጀምሮ እስከ ሕዳር ወር 1971 ዓ.ም. የትግራይ ከተሞች በሰው ደም የታጠቡበት ወቅት ነበር ።የለሊቱ አፍኖ መውሰድና የውሃ ሽታ ሆኖ የቀረው ትግራዋይ ቤቱን ይቁጠረው ፡በዚሁ የከተማው የቀን ሽብር የተካፈሉ መሪዎች 1 አረጋዊ በርሄ 2 ግደይ ዘራፅዮን 3 አባይ ፀሃየ 4 ሥዩም መስፍን ሌሎች ብስራት አማረ- ሳሞራ የኑስ – መለስ ዜናዊ በጣም ፈሪ ስለሆነ አይሳተፍም ስብሃት ነጋ እግሩ አባጣ ስለሆነ መሮጥ ስለማችል ሽማግሌው ። ይህ ሽብርተኛ ቡድን እንዴት ተብሎ ነው የትግራይ ህዝብን መሪ መሆን የሚችለው ፡ የትግራይ ህዝብ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነው ፤ወያኔ ገዳይ ዘራፊ ሽብርተኛ ዘረኛ አምባገነን ነው፤ ስለዚህ የትግራይ ህዝብና ወያኔ አይገናኙም የሚገናኙበት መንገድም የላቸውም የሰማይና የመሬት ርቀት በመሃከላቸው አለ ።

አሁንም ከራስህ አልወረዱም በዘርና በጎጥ ከፋፍለው ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥለው ማየት የሚመኙ የቀድሞ ቁንጮ መሪዎች የነበሩ ባድመና የጎንደር ክ/ሃገር በሱዳን አዋሳኝ ያሉት ታሪካዊና ለም መሬት ከ745 ኪ/ሜትር በላይ ለሱዳን መንግሥት በምሸጥ ግንባር ቀደም የነበሩት በሥልጣ ሽኩቻ በመለስን በስብሃት ነጋ በማለሊት ምስረታ ተገፍትረው የተባረሩ ግደይ ዘራፅዮን እና አረጋዊ በርሄ ሰሙኑ ከኢሮፖ ገስግሰው ኢትዮጵያ ገብተዋል ይዘዉት የመጡ መፈክር በዶ/ር አብይ አህመድ ለኤርትራ የተሰጠው መሬት (ኢትዮጵያውያን የትግራ ህዝብ ለኤርትራ ሸጡን )የትግራይ ህዝብ ቀስቅሰን በሃይል እንመልሰዋለን ብለው ይፎኩራሉ ይህ ቦታ የሸጠው ራሱ አረጋዊ ብርሄ ነው ፡ ይህም በ1972ዓ.ም. የተሸጠው የነበሩ ግደይ ዘራፅዮን ስብሃት ነጋ መለስ ዜናዊ አባይ ፀሃየ ስዩም መስፍን እነዚህ መሪዎች ናቸው ሌላ የሚጠየቅ የለም በወንጀለኛ ተግባራቸውም ይጠየቃሉ ፡ አሁን ነፃ መስለው መናገራቸው ዕብድነት ወይስ ቅዠት ነው ይህ ብቻ ሳይሆንም የትግራይ ህዝብ ቀውስ ውስጥ አስገብተው እንደለመዱት የትግራይን ህዝብ በባርነት ለመያዝና አሸማቅቀው ለመግዛት ለማጥፋት ነው ።

ይብቃህ በጠባብ ብሔርተኞች ከሃዲዎች 43 ዓመት የተሰቃየከው በቃ ብሉህ አስወግደው የባርነት አገዛዝ ነው ፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ከክልል አገዛዝ በቋንቋ በዘር መገዛት ይብቃን እያለበት ያለ ስአት ነው ደፍሬ የምናገርህ ያለህ ስለ ስለሚከነክኝ ነው፤፡ በህ.ወ.ሓ.ት.ማፍያ ሽብርተኛ ቡድን መውደቅህ ለኔ ትልቅ ህመም ነው ኩሩ ህዝብ ሰርተህ የምትገባ ፡ተመልሰህ በእነ አረጋዊ በርሄ እጅ ልትወድቅ ያን ሁሉ ወንጀል የፈፀሙብህ ።እጃቸውን ይዘህ ለፍርድ አቅርባቸው ።እናንተ የወያኔ ካድሬዎች እና ደጋፊዎች የትግራይ ልጆች ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ውረዱ ህዝቡ የሚሰቃየው ያለ በናንተ እጅ ስለወደቀ ነው። ።????????? የትግራይ ህዝብም ይህ ቀይ ምልክት አሳይተህ አስወግዳቸው።

አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የህ.ወ.ሓ.ት.መሪዎች በሰኔ 29/2010 በመቀሌ ከተማ 5ኛ ዙር 12ኛው ጉባኤ የክልሉ የምክር ቤት ጉባኤ አካሂደዋል በመግለጫም ይፋ አድርገዉታ ውሳኔም አስተላልፈዋል ፤ ያሳለፉት ወሳኔ የዛቻና በቀል በኢትዮጳና በኢትዮጵያ ህዝብ ያነጣጠር ጭምርም ነው ፤የወያኔ መሪዎች ድሮም የነበሩ አሁንም ያሉት በትምክህትና በዘረኝነት ኧእምሯቸው የተበከሉ በህዝባዊ አብዮት የሚገኘው ያለ ተራማጅ ለውጥ ለመቀልበስ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ የያዙ የወያኔ የቀድመው ከፍተኛ መሪዎች እነ አረጋዊ በርሄ ኢትዮጵያ ተፋጥነው የገቡት ህ.ወ.ሓ.ት. ከነበረው የበላይነት ሥልጣኑ በህዝባዊ አብዮቱ ተገፍትሮ መጣሉን አሳስብዋቸው የወያኔን ስርአትም ደግሞ ለማስመለስ በዚሁ የመቀሌው ጉባኤ ካስተላለፉት ውሳኔ አንድዋን ቀንጭቤ ላቅርብ፣ በተራ ቁጥር 7 የኢትዮ-ኤርትራ በተመለክተ በሰላም እንዲፈፀም እንቀበለው ሲል ሆኖም ግን ዘላቂ መፍትሄውና ዘላቂ ሰላም ለማግኘት የትግራይ ህዝብ እንዲሳተፍበት፤ ካለ ትግራይ ህዝብ ተሳትፎ ውጤት የለዉም በማለት የትግራይ ክ/መ/ ጥሪወን ያቀርባል ይላል።

ይህ የእነ አረጋዊ በርሄም ሃሳብ ነው፤በዶ/ር አብይ የሚደረገው የአልጀርሱ ውሳኔ ተቃውሞ በ10/06/2018 በልሳናቸው ት.ዴ.ት. በኩል ያወጡት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር የ ‘አልጀሪሱ ውልን ይቃወማል’ ፡ዶ/ር አብይ የአልጀርሱ ስምምነት እንዳለ ተቀብሎ ወደ ተግባራዊ ይሆናል ማለቱ ፀረ ትግራይ ህዝብ ደርጊት ነው በማለት በትግራይ ህዝብ ስም እንደቀድሞ ልማዱ ችግር ለመፍጠር ከግደይ ዘራፅዮን በአዲስ አበበ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ፡በንፁህ ትግራዋይ የፈፀሙት ወንጀል አልበቃ ብላቸውው ከትግራይ ህዝብ ራስ አልወረዱም ይህ ችግር የፈጠረት እነሱ ለጊዛዊ ጥቅም ብሎ የሸጠው ስድስቱ ከፍተኛ መሪዎች ሆነው እያሉ የትግራይ ህዝብ በጉዳዩ ሳይነጋገር ሳይመክር የሚደረግ ያለ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ህዝብ ለኤርትራውያን እየሸጡን ናቸው የሚለው ያለ አረጋዊ በርሄ አዲስ አበባ ተውሽቆ ፤እሱስ በመሪነቱ ከባድመ እስከ ባዳ ትግራይ ከአመራር ጓደኛቹ ሲሸጡ ለትግራይ ህዝብ አማክረው ነው የሸጡት ተደብቀው ነው ለጥቅም ሲሉ ይህን ሁሉ ለከፍተኛ አደጋ የሚዳርግ የፈፀሙት ፡ አሁን በትግራይ ያለው ሽብርተኛ ህ.ወ.ሓ.ት.በእነ አረጋዊ በርሄ በሚመራበት ወቅት ለኤርትራ አሳልፎ የሰጠው ብቻ ሳይሆን በጎንደር ጠ/ ግዛት ውስጥ ለሱዳን መንግሥት ከ745 ኪ/ሜትር በላይ ለሱዳን መንግሥት ሲሸጡ ከባለቤቱ የአማራ ህዝብ ተነጋግረ ነው? አይደለም በሚስጢር ካርቱም ገብተው የኢትዮጳያ ሏላዊ በመፃረር ለጊዝያዊ ጥቅማቸው የሸጡት እነ አረጋዊ በርሄ ?

አማራው አነጋግረው አልሄዱም ፤ድሮውስ የአማራ ህዝብ እኮ ለወያኔ እውቅና አልሰጠም አያውቀዉም ወያኔ ተገንጣ ነው ትግራይ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የተነሳ ፀረ ትግራይም ነው ፤ የትግራይ ህዝብም አልተቀበለውም በጠመንጃ አፈሙዝ የትግራይ ህዝብ እያሸማቀቀ በትግራይ ህዝብ ስም እየነገደ የመጣ ፋሽሽት ድርጅት ነው ።

አሁን እንደ እብድ ውሻ የሚቃዡበት ያሉት ለምን በኢትዮጵያ አዲስ ለውጥ ተፈጠረ ነው፤ አብዮቱን ለመቀልበስ ለውጡን ለማኮላሸተ እንቅፋት ለመፍጠር ሆን ብለው እየፈጠሩት ያለ ዘዴ ነው ፡ ይህ በኢትዮ ኤርትራ የመጣው የስላም የፍቅር የሁለቱ አገራት ጥሩ ግኑኝነት መደጋገፍ አብሮ ተባብሮ መስራት የወያኔ መሪዎች አይፈልጉትም፡ የወያኔዎች ፍላጎት የኤርትራ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም በፍቅር መኖር አይቀበሉትም ምክንያቱም ፀረ ሰላም ፀረ ፍቅር ናቸውና ። በእግዚአቢሄር የተላከ ይህ በክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ እየተመራ ያለው ህዝባዊ የውጥ አብዮት ፡ ወያኔ አሽመድምዶ የጣለው፣ ወያኔ የሚከተለው ዘረኛ ከፋፋይ ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ፡ወያኔያዊ አገዛዝ እያከተመለት ነው ፋሽሽት ወያኔ አብቅተሃል። ኢትዮጵያና ህዝብዋ ወደ አንድነት በፍቅር በሰላም አንድነታቸው ኢትዮጵያዊነታቸው ያረጋገጡበት በለውጡ ጎደና ናቸው በሃገራችን መስረታዊ አዲስ የለውጥ የዲሞክራሲ ስርአት ይመጣል፡ኢትዮጵያ ሃገራችና ህዝብዋ ከወያኔው ፋሽሽታዊ ዘረኛ ሽብርተኛ አገዛዝ ነፃ በመውጣት በፈጣን ጉዞ መንገድ ናት የወያኔ መቃብር ጉድጓድም እየተቆፈረ ነው ።

በኤርትራና በኢትዮጵያ ወንድማሞች ህዝብ የአብሮነት የሰላም የፍቅር የአንድነት በሩ ተከፍተዋ በውጭ በሃገር የሚገኝ ኤርትራዊ ኢትዮጵያዊ እግዚአብሄር ይመስገን ሰላሙ ፍቅሩ ቤታችን ወስጥ ገባ ከእንግዲህ ወዲህ ከእንድነታች የሚያፈናቅለን የሚለየን ኋይል የለም ፤ ወያኔ የፈጠረው በኤርትራ ህዝብ በኢትዮጵያ ህዝብ የቅራኔ ግንብ ፈርሶ ድምጥማጡ ጠፋ ።

1ኛ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጥቃቱ በትግራይ ህዝብ እንደ ጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ በ1969 ዓ.ም ተከትሎ የመጣ ፤ የወያኔ መሪዎች ተሰባስበው በሊቀ መንበሩ አረጋዊ በርሄ መሪነት በነፃ መሬታችን የሚገኝ መጤ የሆነ ሁሉ ከትግራይ መውጣት አለበት ብሎ ከወሰነ በኋላ ለህዝብ ግንኙነት ሁሉ ትእዛዝ ተላለፈ ፡፡በድርጅቱ ውስጥም ትግራይ ተወልደው ያደጉ ታጋዮች ነበሩ በየከተማው ብዙ ናቸው ሆኖም በድርጅቱ ውስጥ ብዙ ቅሬታ ፈጠረ ፡ይህ ትእዛዝ የተቀበለው የህዝብ ግንኙነት አባላት በየወረዳው በየቀበሌው የሚገኙ አማራ ኦሮሞ ውጡ ትግራይ ለትግራዋይ ብቻ ናት ብለው ንብረታቸው ሁሉ እየተወረሰ ባዶ እጃቸው ወጥተው ወደ ትግራይ አውራጃዎች ገቡ የተገደሉም አሉ። ትንሽ ቆየት ብለውም ኢ. ህ አ. ፓ በደብዳቤ ተፅፎ ትግራይ የትግራዋይ ብቻ ስለሆነች ውጣ ተባለ ፤በደብዳቤ መልሶ የላከው ኢ.ህ.አ.ፓም ድርጅታችን የሚያውቀው ትግራይ ኢትዮጵያዊት የሁሉ ኢትዮጵያ ናታ አንወጣም በማለት መልስ ላከ።ህ.ወ.ሓ.ት. ሁሉ ዓይኑ ወደ ወልቃይት ፤ጠገዴ፤ጠለምት ፤ቃፍታ ሁመራ በጉልበቱ ወሮ ለመያዝ በወሎ ጠ/ግዛትም ከላይ ሓሸንጌ እስከ ራያና ቆቦ ወሮ ለመያዝ ባስቀመጠው የመስፋፋት ፖሊሲው በዝግጅት ላይ ነበር፡ በተለይ በሰሜን ጎንደሩ አማራ ወልቃይት ጠገዴው ከህዝቡ የሚደርሰውም አፀፋዊ ምላሽ ወያኔ ስለማይችለው ፤ የአማራ ህዝብ በተገኘበት አፍኖ መውሰድ እንዲገደል ከላይ በተጠቀሱ የወያኔ መሪዎች የታወጀው፤ በጀመረው 1969 ዓ.ም. ነበር ።

2ኛ ለሱዳን መንግሥት ህ.ወ.ሓ.ት. የሰጠው መሬት ከ745 ኪ/ሜትር ርቀት ያለው ለምና ድንግል ብዙ ጫካ- ወንዞች የተፈጥሮ ሃብት የተሸከመ – የተለያዩ እንስሣት ያሉበት- የኢትዮጵያ የጎንደር ጠ/ግዛት መሬት ሱዳን የሚያዋስን ሁሉ ነው ።ታሪካዊም ነው ገናናው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አጼ ቴድሮስ በመቅደላ ፤ አጼ ዮውሃንስ በመተማ ከእንግሊዝና ከማህዲስት ወራሪዎች በተካሄድ ጦርነት ሁለቱ የኢትዮጵያ ነገሥታት መስዋእትነት የከፈሉበት፡ታሪካዊ የኢትዮጵያ ግዛት ። ይህ ሕገ ወጥ ፀረ ኢትዮጵያ ሏአላዊነት ወያኔ አሳልፎ ለሱዳን መንግሥት ጊዝያዊ ጥቅም ለማግበስበስ ሲሉ በወቅቱ የሱዳን መንግሥት ርእሰ ቢሄር ከነበሩት ጀነራል ጃእፈር ኒሜሪ ሌሎች የሱዳን ባለ ሥልጣናት መስከረም ወር 1975 ዓ.ም. የወያኔ መሪዎች

1 አረጋዊ በርሄ

2 ግደይ ዘራፅዮን

3ስብሓትነጋ

4መለስዜናዊ

5አባይፀሃየ

6ሥዩምመስፍን፤ ከሱዳን መንግሥት ባለ ስልጣናቱ ካርቱም ከተማ ተገኝቶው ባካሄዱት ስብሰባ የሱዳን ግዛትና መሬት ነው ብለው ፈርመው ለሱዳን መንግሥት ያስረከቡት ጊዜ ነው።

የዚሁ አሳፋሪ ተግባር የወያኔ በዝርዝር ህ.ወ.ሓ.ት.ና ኢትዮጵያ በሚል አርእስት በግልፅና በዝርዝር ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚመለከተው ባለ ጉዳዩ በህዳር 2010 ዓ.ም. አቅርቤ አለሁ ። ሃገር ሸያጭ ደላላው ወያኔ ፤ኢትዮጵያ በወረራ የነጠቀችው(የያዘችው) የሱዳን ግዛት መሬት መሆኑ በቀረበው ማስረጃ ስለተረጋገጠልን የሱዳን መሬት ነው በማለት አስረከበ ።ይህም ተግባራዊ የሚደረገ ፤ትግራይ ከአማራው ጨቋኝ ስርአት ነፃነትዋ ተቀዳጅታ የራስዋ መንግሥት በምትመሰርትበት ጊዜ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ተደመደመ ።

በዚሁ የሚነሳ መነሳትም ያለበት ጥያቄ አለ ?//ይህ ወያኔ አሳልፎ የሸጠው የጎንደር ጠ/ግዛት የኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ነው// ወያኔ ደግሞ ትግራይ ለማስገንጠል ብሎ የደደቢት በረሃ የሽብር ነፍጠኛ ነው // 1ኛ ማን በምን መልኩ የጎንደር ጠ/ግዝት የኢትዮጵያ ሏአላዊነት ለሱዳን መንግሥት ለመሸጥ ምን መብትና ሥልጣን ነበረው ህ.ወ.ሓ.ት.? በማን ተወክሎ ? ይህ የጎንደር ጠ/ግዛት መሬት ነው ወያኔም በዚሁ ቦታ ማንም የሚያውቀው የለም ማንም ወረበላ ማፍያ በምን መልኩ ስለ ሃገር ይደራደራል የሱዳን መንግሥት ለምን ይህ ድርድር አመነበት ? 2ኛ የሱዳን መንግሥት ከማንም ፀረ ቡድን ውል አለኝ አሁን በአማራው ህዝብ እያካሄደው ያለ ጥቃት ከወያኔ ተባብሮ ህ.ወ.ሓ.ት.እና የሱዳን መንግሥት ሕገ ወጥ መንገድ ይዘው የኢትዮጵያ ሏላዊነት እየወረሩ ናቸው //ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በመሬቱ ግዛት ውስጥ በመግባት ጥቃት በመሰንዘር ህዝብን አስቸግረዋል ? ።

ይህን ለሚመለከተው ለተ.መ.ድ. ካለ እረፍት ደጋግመህ አቤቱታ ማቅረብ ። ከዚሁ ጊዜ ከመስከረም ወር 1975 ዓ.ም. ህ.ወ.ሓ.ት. የሱዳን መንግሥት የዓይን ቢልየን ከመሆን አልፋ የበህር ልጅ እስከ መሆን ደረሰች ።ከዚህ በመነሳት የሱዳን መንግሥት ለህ.ወ.ሓ.ት. ከፍተኛ ውለታ ውሎለታል በሙሉ አቅሙ ወያኔ የረዳ የተባበረው የሱዳን መንግሥት ሆነ ፤አሁንም ጭምር። የዚሁ ውጤት ደግሞ ዛሬ እየታየ ያለው የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች በመስከረም ወር 1975 ዓ.ም. ለጊዜያዊ ጥቅም በለው አሳልፈው የሸጡት፤ የሱዳን ወራሪ ሃይል ኢትዮጵያዊ የአማራ ህዝብ፤ ይህ የሱዳን መሬት ነው ውጣ ልቀቅ እያሉ ከወያኔ ሠራዊት በመተባበር ህዝብ እየገደሉ ፤ህዝብ ከትውልድ መሬቱ እያፈናቀሉ ለችግርና ለመከራ ዳርገዉት ሱዳንና የወያኔ ስራዊት እያሰቃዩት ይገኛሉ ።

ህ.ወ.ሓ.ት. በ1983 ዓ.ም. በግንቦት ወር በለሱ ቀንቶባቸው ኢትዮጵያን ወረው በቅኝ አገዛዛ ሲኦል ስርአታቸው ከወደቀች ለ27 ዓመት ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለባርነት አገዛዝ የወደቀበት ከተወለደበት መሬቱ በሃይል መሬት የመንግስት ነው እየተባለ ተፈናቅሎ በረሃ ወድቆ መኖሪያ ቤቱ ተነጥቆ መጠለያ በማጣት በርሃብ በበሽታ ህዝብ እንዲያልቅ ተደረገ በብዙ ሚልዮን ኢትዮጵያዊ ለስደት ተዳረገ ፤ሽብርተኛ ፤ቦዘኔ፤እየተባለ በማሰር በመግደል በዙ ግፍና ሰቆቃ በህዝብ ወረደ የወያኔ ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ የወረደ ህዝብ፣ በሲኦል አለንጋ ለ27 ዓመታት በፋሽሽት ሽብርተኛው ናዚ ወያኔ የግፍ ግፍ በኢትዮጵያ የፈፀመ ህ.ወ.ሓ.ት. ነው ።

ህ.ወ.ሓ.ት. ለሽህ ዘመናት ተከብሮ የቆየ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት የደፈረ የሸጠ ፀረ ሃገር ፤ ሃገር በቀል ክፉ ደመኛ ጠላት ነው፤ኢትዮጵያ ዳር ድንበርዋ ተደፍረዋል ።በዚሁም ላይ ተስፋፊው ህ.ወ.ሓ.ት. ፤ታላቅዋን ትግራይ ለመፍጠር ሲል የሰሜን ጎንደር ፤ የጎንደር ጠ/ግዛትና የትግራይ ጠ/ግዛት በተከዜ ወንዝ የተካለለ ጥንታዊ በኢትዮጵያ ታሪክ ግዙፍ እውቅና ያለው ድንበር ተሻግሮ በጉልበቱ፤ ወልቃይት ፤ ጠገዴ ፤ጠለምት ፤ቃፍታ ሁመራ የትግራይ ነው በማለት ብዙ ሚልዮን አማራ ዘሩን በማጥፋት Genocide በአሳዛኝ ሁኔታ ከላይ የተጠቀሱ የወያኔ አመራር በተለይ 6ቱ ከታህሳስ ወር 1972 ዓ.ም.ጀምሮ የአማራ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አጥፍተዉታል ገድለዉታልም ፤ቀሪው ደግሞ በስደት ተበታተነ፤እዛው የቀረው የወልቃይት ጠገዴ አማራም መሬቱ ተነጥቆ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ የስቃይ መከራው ይገፋል ።በደቡብ ወሎም ከአሸንገ እስከ ራያና ቆቦ ወያኔ በጉልበቱ ሰፊና ለም መሬት በተስፋፊነት ባህሪው የትግራይ ነው ብሎ መሬቱ ዘርፎ ወደ ትግራይ አስገብቶታል ።
በአጠቃላይ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራር በሙሉ የመጀመሪያዎቹ በዋናነት የአማራ ዘር እያጠፉ የመጡ ተከታትለው የመጡም እስከ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አሁን ያለው የትግራይ ፕረዚዳንት አማራው አጥፍተዉታል።

ከ1967 ዓ.ም.እስከ አሁን 33 የሥራ አስፈፃሚ ደርሰዋል እነዚህ ሁሉ በአማራው ላይ ዘሩ ማጥፋት ትልቅ ሚና የተጫወቱ ፡ወንጀለኞች በከባድ የወንጀል ሕግ የሚጠየቁ ፀረ ኢትዮጵያ ናቸው።ከ5 ወር በፊት በዘረጋሁት ሰፊ ፅሁፍ “በዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው “በሚል አርእስት ለኢትዮጵያ ህዝብ የህ.ወ.ሓ.ት.ፋሽሽት ሽብርተኞች በኢትዮጵያ ህዝብ ፤በሃገር ሏአላዊነት የፈፀሙት ዝርዝር ገበና አቅርቤ አለሁ ።ማንበቡ በርካታ ግንዛቤ ይገኝበታል ። የጠላትህ ማንነት የምታውቀው!ስታነበው ስትመለከተው ነው ።

በህ.ወ.ሓ.ቱ መለስ ዜናዊ እየተመራ የመጣው ወራሪ ቅኝ ገዢ የማፍያ ጉጅሌ ወያኔ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያና ህዝብዋ በእጅ መዳፍ ወድቃ ለ27 ዓመታት በህ.ወ.ሓ.ት.ፋሽሽታዊ ሽብርተኛ ዘረኛ አገዛዝ በአረሜናዊ (barbaric) የናዚ ስርአት ኢትዮጵያዊ ህዝብ የተሰቃየበት የጨለም የባርነት የአገዛዝ ዘመን ሆኖ የቆየበት ነው ። የርሃብ የበሽታ የስራ አጥነት የስደት የሞት በቶርቸር አሰቃይቶ መግደል ማሰር ፤ ህዝብ ከትውልድ መሬቱ ማፈናቃል ህዝብ ከቦታው አፈናቅሎ ለቱጃር ዓረቦች መሽጥ። ለዚሁ የወያኔ ፋሽሽት ስርአትም መግለጫ አይገኝለትም ። 27 ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ደም ያለቀሰበት ልጆቹ በየበረሃ ሞቶው የቀሩበት ተበታትነው ጠፍተዋል፤ የባንዳው መለስ ዜናዊ ስርአት ፤የኢትዮጵያ ወጣቱ ዜጋ ሴት ወንድ ብኩን ከንቱ ስንኩል ሆኖ እንዲቀር ያወጣው ፖሊሲ በኢትዮጵያ ውስጥ ሃሺሽና አደንዛዥ እፆች(Drug )በስፋት በየገበያ እንዲስፋፉ በማድረግ ሆን ብለው ወጣቱን ዜጋ የሃገር ተስፋ ብዙ እንዲበከል አድርገዋል። ሽርሙጥና እንዲስፋፋም አድርገዋል ።
ሌላው በአማራው ክልል የአማራው ዘር ባጭሩ ለመቅጨት የዓይን ትራኮማ ወ.ዘ.ተ. እየተባለ ወጣት ወንዶች ሴቶች በየትምህርት ቤቱ በሌላ በሽታ ታመው ለሚመጡ ይህ ወሊድ የሚዘጋ አምካኝ መድሃኒት በስፋት ተጠቅመውብታ በዚሁ የተነሳም በዙ የአማራ ወጣቶች መሃን ሆነው ቀርተዋል ።

ይህ የወያኔ ሤራ የአማራው ዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ።ይህም በዓለም አቀፍ ሕግ ይጠየቁበታል ።
ህ.ወ.ሓ.ት. እና የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮት //
ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮት የተጀመረው ገና ወይኔ በረሃ በነበረበት የጎንደር ጠ/ግዛት የሰሜን ጎንደር ለም መሬት ወደ ትግራይ ለማስገባት የትግራይ ግዛት(ክልል) ለማድረግ ሙሉ ሃይሉ የወያኔ ስራዊት አጅቦ ወልቃይት፤ ጠገዴ ፤ ጠለምት ፤ ሁመራ ፤ለመውረር በግፈኛ ወራሪና ተስፋፊው ህ.ወ.ሓ.ት. በወርሃ ታህሳስ 1972 ዓ.ም. ተጠናክሮ ወረራው በማካሄድ ብዙ የአማራ ደም የፈሰሰበት የአማራው የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ = የሰሜን ጎንደር ህዝብ ተበታትኖ በወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ላይ በተለያየ ዘዴና የብልሃት መንገድ ጥቃት በመሰንዘር ካለ ማቋረጥ እንሆ እስከ አሁንዋ ስአት ለ40 ዓመታት የአማራው ህዝብ እጁን ሳይሰጥ ወንድ ሴት ሳይለያዩ በአንድነት ሆነው ትንሽ በትንሽ ወያኔ እያዳከሙ የመጣበት ጊዜ አሁንም እየቀጠለበት ያለ ነው።አማራው የሚከተለው የትግል መንገዱ የአማራ ማንነታችን መብታችን፤ ሰሜን ጎንደር ትውልድ ቦታችን መሬታችን በወራሪው ወያኔ ተነጥቀናል እኛ አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም ፤ባህላችን፤ቋንቋች አማራ ፤ድንበራችን ተከዜ ነው፡ ብሎ የተነሳው ከዚህ ወቅት ጀምሮ ነው ። በትክክል ይህ የአማራ ህዝብ ለ40 ዓመት የታገለለታ አሁንም እየታገለለት ያለው ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የደገፈው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ያሳተፈ ትግል ሆኖም መቀጠል የግድ ስለሚል ነው ፡ እውነተኛ ፍትሃዊ የማንነት መብት የአቋም ፖሊሲ በመሆኑ። በወሎ ጠ/ግዛትም የህ.ወ.ሓ.ት.የመስፋፋት ፖሊሲ ከሓሸንጌ እስከ ራያና ቆቦ የወሎ ህዝብ የማንነቱ መብቱ ተገፈዋል ተነጥቀዋል ። ይህም የመብትና የማንነት ጥያቄ ነው፡ይህን የሚቀለብስ ሕግ በዚች ዓለም ውስጥ የለም ። ክብር የሚሰጠው የዲሞክራሲ የመብት ጥያቄ ሕጋዊም ነው ።

human right declaration በሕገ ወጥ የሚገልፀው በተስፋፊነት የሌላውን የማይገባው የመሬት ወረራ የፈፀመ ህዝብን ያፈናቀለ ወንጀለኛ Genocide ስለሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ በከባድ ወንጀል ይጠየቃል ነው የሚለው ።ይህንና ሌላ በርካታ ፀረ ሃገርና ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ ፀረ ዲሞክራሲ ሆኖ ለ43 ዓመታት የመጣው ወንጀለኛው ህ.ወ.ሓ.ት. አሁን በከፍተኛ መስዋእትነት እየተገኘ ያለው የሁሉ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮት የለውጥ ጎደና አልቀበልም ብሎ ትግራይ ውስጥ መሽጎ ብዙ የሤራ ምግባራቱ እየሰራ ይገኛል ።

ህዝባዊ አብዮቱን ለመቀልበስ እንቅፋቶች እየፈጠረ ይገኛል ። ለ27 ዓመታት በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ኢትዮጵያን የገዛ ፋሽሽታዊ ስርአት ዘርግቶ ኢትዮጵያና ህዝብዋ ለከፍተኛ አደጋ የዳረገ ህ.ወ.ሓ.ት. ተፈጥራዊ ባህሪውም ይህን አብዮት ለመቀበልም አይፈቅድለትም ምክንያቱም 1ኛ ህ.ወ.ሓ.ት. ከአፈጣጠሩ ፀረ ዲሞክራሲና ፀረ ማንነት ፀረ መብት ነው 2ኛ ዘረኛ ጎጠኛ ጠባብ ብሄርተኛ ነው 3ኛ ሽብርተኛ ድርጅት ፀረ ህዝብ ነው 4ኛ ጸረ አንድነት ከፋፋይ ድርጅት ነው 5ኛ ፀረ ኢትዮጵያ አንድነትና ፀረ ሏአላዊነት ነው ኢትዮጵያዊነት ያወገዘ ገና ሲፈጠር ነው 6ኛ ድርጅቱ የመሻሻል አቅም የሌለው በድን ሆኖ የተፈጠረ በጣም አደገኛ አወናባጅ ስለሆነ ጥንቃቄ ሲበዛም አስፈላጊ ነው፣አመራሩ የድሮዎቹም የአሁኖቹም ሁሉ በሃገርና በህዝብ ጠልነት የተመረዙ ናቸው ። ወ.ዘ.ተ. በእነዚህ ባህሪያት የተመረዘ ድርጅት የህዝብ አብዮት ከመደገፍ ይልቅ አብዮቱን ለመቀልበስ ወደ ሚሰራበት ፀረ አብዮት ተግባሩ ይሰማራል ። ለዚሁ ተግባሩም አብነቶች ልጥቀስ ፤የለውጡ መሪ ነብዩ በእግዚአቢሄር ፈቃድ ኢትዮጵያና ህዝብዋ አድን ተብሎ የተላከው ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስተር የህ.ወ.ሓ.ትን የ27 ዓመት.ፋሽሽታዊ አገዛዝ አብቅቶ ህ.ወ.ሓ.ት. ጓዙን ጠቅለሎ ትግራይ ሂዶ ሲመሽግ እዛ ሆነው በዙ ተንኮልና ሤራ በመዶለት ዶ/ር አብይን ለመግደል በሰኔ 16/2010 መስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ የወያኔ ገዳይ ቡድን በማሰማራት ቦምቦች በማፈንዳት ሁለት ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ 164 ኢትዮጵያውያን ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ አድርሰዋል ዋናው የግድያው ታርጌት የነበረው ዶ/ር አብይ አህመድ ነበር ፤አምላክ አዳነው ።

የህ.ወ.ሓ.ት. /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሕገ መንግሥት ተጣሰ ፤ባለ ኮኮብ የኢ.ፈ.ዴ.ሪ ባንዴራ ተጥሎ የቀድሞ ባንዴራ ህዝቡ እየተጠቀመ ነው ፤የኢ.ፈ.ዴ.ሪ. ፈደራሊዝም ወደቀ ፤ህ.ወ.ሓ.ት. ለ17 አመት ታግሎ ያመጣው የብሄር ብሄረሰቦች መብት ያረጋገጠው እየተናደ ነው ፤ኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ማእከል ያደረገው ሕገ መንግሥት ተጣሰ እያለ ወያኔ ለውጡን በማውገዝና በመኮነን ሲገኝ ጎን ለጎን አብዮቱን ለማደናቀፍ እየሰራ ይገኛል ። አሁን የወያኔ መሪዎች እያደረጉት ያሉ ቀድሞ በ1977 ዓ.ም. መጨረሻ በ1993 ዓ.ም በመለስ ዜናዊ እና በስብሃት ነጋ ስየ አብርሃ አባይ ፅሃየ በስልጣን ሽኩቻ የተባረሩ ፖሊት ቢሮ (ሥራ አስፈፃሚ ) የቀድሞዎቹ በገንዘብ በተለያዩ የነዋይ ጥቅም ደልለው ሁሉን በማሰባሰብ ትግራይ ገብተዋል ለመንግስት የሚሉት የለውጡ ደጋፊ ነን እያሉ ፤ ሓቁ ግን ለማታለል የተጠቀሙበት ዘዴ ነው ።ቀናት ሳይቆዩ በራሳቸው አንደበትም ማንነታቸው ሲጋለጡ ትግራይ ሂደው ይሁን አይሁን በሚድያ የሰማሁት ፤ አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘራፅዮን እነዚህ ኮተታሞች በሓምሌ 10/2010 ከድምፂ ወያኔ ጋር ባካሄዱት ቃለ መጠይቅ በግልፅ የተናገሩት በትግራይ ህዝብ ግፍ እየተፈፀመ ስለሆነ የአልጀርሱ ስምምነት በተግባር በዶ/ር አብይ ይፈፀማል ማለቱ ተቃውመን ነው ፡በሩጫ ኢትዮጵያ የገባነው ሲሉ ሌላው ጥያቄ በጋዜጠኛው የቀረበላቸው ደግሞ በዋናነት እናንተን ለማነጋገር ከህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ተልከን የመጣነው ፤ አሁን የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ከእናንተ ተባብሮ መስራት ይፈልጋል ይህን ትቀበሉት አላቹህ ? ብሎ ሲጠይቃቸው በቀጥታ፣ የሰጡት መልስ ፣ይህ እኛ የምንፈለገው ነው የመጣነው ለዚሁ ነው በደስታ ተቀብለነዋል” አረጋዊ በርሄ “፡ቀጥሎም ግደይ ዘርአፅዮን ከህ.ወ.ሓ.ት አመራር ያባረሩን እነሱ ናቸው ያጠፋነው ጥፋት የለንም አንድ ሁነን ተባብረን የትግራይ ህዝብ እንመራው ነበርን ፡ አሁን ይዘኸው የመጣህ መልእክት አረጋዊም እንዳለው በደስታ ተቀብለነዋል፣ ድሮውም አብረን ህ.ወ.ሓ.ት በምንመራበት ጊዜ ልዩነት አልነበረንም አንድ ነበርን በድንገት ሳናስበው በሥልጣን ሽኩቻ አባረሩን ያጠፋነው ጥፋት የለንም።

ደጋግመው ሁለቱ የድሮ መሪዎች አፅናኦት በመስጠት በአንድነት ተቀላቅለን ለመስራት የፍላጎታችን መለክት በቶሎ አድርስልን በማለት ተማፅነው ተሰናበቱ። ስወስቱ (3ቱ) የድምፂ ወያኔ ጋዜጦኞቹም አሁን እናደርሳለን ብሎ ሄደ። በአንድ ራስ ሁለት ምላስ የሚባለው ይህ ነው ፣ኢሮፓ እያሉ የሸንጎ ድርጅት ሽፋን አድርገው ምን ይሉ ነበር ፣አዲስ አበባም ገብተው እኛ የመጣነው ለውጡን በመደገፍ ለጠ/ሚኒስትሩ ለማማከር ለመርዳት ነው፣እያሉ ሲያጭበረብሩ ሳምንት ሳይሞላቸው ፣በትግራይ ህዝብ እየደረሰበት ባለው ችግር ለመከላከል ነው ኢትዮጵያ የገባነው አሉ።የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ናዚ ስርአት የደረሰበት ግፍና ሰቆቋ ወደ ኋላ ገሸሽ አርገው በመጣል።አሁን ያ የገደሉት ያጠቁት ሃብት ንብረቱ የዘረፉት ከሰባዊ ፍጡር ውጭ ያደረጉት፣ ለትግራይ ህዝብ ዛሬ ተቆርቋሪ አሳቢ መስለው መቆማቸው የሚያሳዝን ነው ።

እናንተ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ከመጀመሪ 1967 ዓ.ም. እስክ አሁንዋ 2010 ዓ.ም. ያላቹህ በሙሉ

1ኛ አረጋዊ በርሄ

2ኛ ግደይ ዘርአፅዮን

3ኛ ስብሃት ነጋ

4ኛ አባይ ፀሃየ

5ኛ ሥዩም መስፍን

6ኛ ስየ አብርሃ

7ኛ አውዓሎም ወልዱ

7ኛ ገብሩ አስራት

8ኛ አርከበ ዕቁባይ

9ኛ ፃድቃን ገብረተንሳይ

10ኛ ተወልደ ወልደማርያም

11ኛ አረጋሽ አዳነ

12ኛ

13ኛ ቴድሮስ ሓጎስ

14ኛ ገብረአብ ባርኖባስ

15ኛ ፀጋይ በርሄ(ሃለቃ)

16ኛ ቴድሮስ አድሓኖም

17ኛ አዜብ መስፍን

18ኛ አበበ ተክለሃማኖት

19ኛ አባይ ወልዱ

20ኛ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

21ኛ ዶ/ር ስሎሞን ዕንቋይ

22ኛ ትርፉ ኪዳነማርያም

23ኛ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአቢሄር

24ኛ ጌታቸው አሰፋ

25ኛ አባዲ ዘሞ

26ኛ አዲስ አለም ባሌማ

27ኛ በየነ ምክሩ

28ኛ ገብረመስቀል ታረቀ

29ኛ ሙሉጌታ አለምሰገድ

30ኛ ዓለም ገብረዋህድ ።

የሞቱ 1 መለስ ዜናዊ 2 ክንፈ ገብረመድህን ።ከነዚህ በተጨማሪ የሚፈለጉ

1 ብስራት አማረ

2 ሓሰን ሹፋ

3 ታደሰ መሰረት

4 ዘራይ አስገዶም

5 ቢተው በላይ

6 ዘራይ ይሕደጎ

7 መኮነን ገብረማሪያም

8 አስመላሽ ው/ሚካኤል

9 አራንሺ

10 ተስፋይ አፈርሰው

11 ተስፋይ ጡሩራ ወ.ዘ.ተ. በኢትዮጵያም ሆነ በአለም አቀፍ በከባድ ወንጀል የምትጠየቁ፡

1 – የዘር ማጥፈት ወንጀል በተግባር ፈፅመዋል በተለያዩ ዘዴዎች በፕላን ሆን ተብሎ በአሰቃቂ ሁኔታዎች የአማራው ህልውና አጥፍተዋል አሁንም እያጠፉት ነው፡ በኦሮሞ- በጋምቤል- በአኝዋክ ወ.ዘ.ተ.

2- የኢትዮጵያ ህዝብ ለሕገ ወጥ ተግባራቹህ አፈናቅለዋል 3- የኢትዮጵያ ሏአላዊነት አፍርሰዋል ሽጠዋል ለምሳሌ የአማራ መሬት ለሱዳን፣ በኤርትራ ድንበር ያሉት አካባቢ

3- የአማራው ኩሩ ኢትዮጵያዊ የመብት ማንነቱ በህ.ወ.ሓ.ት መስፋፋት ፖሊሲ መሰረት ሙሉ በሙሉ ተጥሰዋል።

4- ኢትዮጵያ ና ህዝብዋ በዘር በቋንቋ ከፋፍለው ታላቅ ሃገር አሁን ለደረሰችበት ወድቀት ደደቢት በረሃ ባዘጋጁት ማኒፈስቶ ለዚሁ ክፉ አደጋ አድርሰዋታል፣

5- በጠቅላላ የኢትዮጵያ ሃብት ንብረት ወርቅ -ገንዘብ ዘርፈዋል ፡6- የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ሀ-እስልምና ሃይማኖት ለ- የኢትዮጵያ ተዋህዶ ከርስትና ደፍረዋል የእምነት ተከታይ ህዝብ ምእመናኑ ከፋፍለዋል

7- የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች የጥንት የታሪክ መፃህፍት ታሪካዊ ሰነዶች ዘርፈው ሽጠዋል፣ አቃጥለዋል ፡

8- የኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተቋማት ( የአንዲት ሃገር የኢኮኖሚ እስትራቴጂ )

1-ባንኮች

2- የኢትዮጵያ አየር መንገድ

3-ትራንስፖርት የብስ 4- የሃገር ማአድናት በሙሉ

5- መብራት ሃይል

6- ኢትዮጵያና መሬትዋ ( መሬት የመንግሥት ነው ተብሎ ) ወ.ዘ.ተ. በእነዚህና በሌሎች የህ.ወ.ሓ.ት. አመራሮች በኢትዮጵያና በህዝብ ወንጀልና ክህደት ፈፅመዋል ። ስለዚህ የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ሁሉ በሃገርና በህዝብ ለፈፀሙት የ43 ዓመት ወንጀለኛ ተግባራቸው በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ይጠየቁ።

ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ //ደምህ አፍሠስህ አጥንትህ ከስክሰህ ለብዙ ሺህ ዓመታት ከወረሪ ጠላት ተከላክለህ ጠብቀህ ያቆየሃት ውድ እናት ሃገርህ ኢትዮጵያ ከደደቢት በረሃ ሸምቀው የመጡ ሃገር በቀል አረሜኔ ጠላቶች ከላይ በዝርዝር ስማቸው የተጠቀሱት የወያኔ ወረበላዎች ለፍርድ አቅርባቸው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ – ይህ አብዮት ለማግኘት ለማምጣት ለ27 ዓመት ያገኘኸው- መከራ – ሶቆቃ-እስራት -ግድያ-መፈናቀል-ርሃብ -በሽታ-መንገላታት-የባርነት-ሲኦል-የናዚው ቅኝ አገዛዝ ራስህ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ታውቀዋለ፡ አከርካሪን ሊሰብርህ የመጣ የወያኔ ስርአት በማያቋርጥ ትግል ታግለህ የወያኔ አከርካሬ ወገቡ ቆርጠህ የጣልከው አንተ ነህ ፡ ሁሌም ድል የሰፊው ህዝብ ነው// አሁን እያገኘኸው ያለ አንፀባራቂው የድል ጉዞህ ፋሽሽቱ ወያኔ ይህን ህዝባዊ አብዮት ለማሰናከል ከቻለም የድሮ የናዚ ስርአቱን እንደገና ለማስመለስ ድብቅ ሤራና ተንኮል ከመፈፀም ወደ ኋላ አይልም።

የኢትዮጵያ ህዝብ የለውጡ መሪው ዶ/ር አብይ አህመድንና ሌሎች አባላት የለውጡ መሪዎችን የያዝከው ሙሉ ድጋፍህና ከለላ ሁነህ ጠብቃቸው። ኢትዮጵያና ህዝብዋ ከፋሽሽት ወያኔ ስርአት ታግለን ነፃ መውጣት ታሪካዊ ሃላፊነትም ግዴታችን ነው።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል/

ድል የሰፊው ህዝብ ነው////

LEAVE A REPLY