“የመፃተኛው ኑዛዜ” | ከበውቀቱ ስዪም

“የመፃተኛው ኑዛዜ” | ከበውቀቱ ስዪም

ካገር ጫፍ እስከ ጫፍ በጥላህ ከልለህ
ተራራው የኔ ነው ለምን ትለኛለህ?
ወንዙ ድርሻዬ ነው ለምን ትለኛለህ?
እንኳንስ መሬቱ አንተም ያ’ንተ አይደለህ፡፡
:
እኔ መፃተኛ አንተ ኗሪ ነኝ ባይ
እኔ እግሬን ስከተል ርስትህን ስታይ
ስቀርብህ ገፋሀኝ ስትገፋኝ ቦታ አጣሁ
ድንኳን ብትተክል፤ ነፋስ ሆኜ መጣሁ፡፡
:
ያ’ባትህ ያ’ባቴ
ጠበኛ ስማቸው
ጠበኛ ህልማቸው
በህይወት ተጣሉ ፤ ታረቁ ባፅማቸው
ባ’ፈር ተቃቃሩ አፈሩ አስማማቸው
በዙሪያቸው በቅሎ ከቧቸው ሞት ደኑ
መተቃቀፍ መርጠው ማማና ወይን ሆኑ፡፡
:
ይችላል ይሉሀል ፍልሚያ ማዘጋጀት
ያ’ባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት
አንተው ጦር ወርውረህ አንተው ቀድመህ ወደቅህ
አካሌ ደረቴ መሆንህን መች አወቅህ?!

LEAVE A REPLY