የሸገር ልጅ ዜማ | በፍቃዱ ዘ ኃይሉ

የሸገር ልጅ ዜማ | በፍቃዱ ዘ ኃይሉ

ልብሴ እየወበቀኝ፥ ቆዳዬ እየሞቀኝ
“ከተማው የማነው?” ብሎ ቢጠይቀኝ
ጥርሴ እስኪረግፍ ነው፥ ማርያምን ያሳቀኝ።

ስንትና ስንት ዓመት፥ ለዕድሜዬ እኩሌታ፣
ያደግኩበት አገር፥ የኖርኩበት ቦታ፣
መቆሚያ የሌለኝ፥ እኔ የአገር ችስታ፣
ከተማን የሚያክል፥ ግዙፍ የአገር ክፋይ፣
ግዙፍ ያገር ዋልታ፣
“የኔ ነው”፣ “የእሱ ነው” የሚያስብል ጫወታ፣
ኬ’ት ነው ያመጣብኝ፥ የሠራዊት ጌታ!? 😂😂

“ፊንፊኔ ኬኛ” ይለኛል፥ ይኼ ከመሬት ተነስቶ
“በረራ የኛ” ይለኛል፥ ሌላኛው መላሽ በቀረርቶ፣
የምትቆምበት ባገኘህ፥ የምትነግሥበት ቀርቶ!

LEAVE A REPLY