ትናፍቂኛለሽ || በፍቃዱ ዘ. ኃይሉ

ትናፍቂኛለሽ || በፍቃዱ ዘ. ኃይሉ

እንደ ልጅነቴ፥ እንደ ደጉ ዘመን
እንደ‘ማይመለስ በገበያው ተመን

ትናፍቂኛለሽ፣
እንደ አገሬ ፍቅር፥ ሳያልቅ እንዳለቀው
ውሉ እንደ ጠፋብኝ፥ ሴራ እየሰረቀው

ትናፍቂኛለሽ፣
እንደ አዲስ አበባ፥ እንደ ሥሟ ብዛት
ብዙ እየተመኘ፣ ማንም የማይገዛት

ትናፍቂኛለሽ፣
እንዳለፈው ጊዜ፥ ካለፈ በኋላ እንደሚፀፅተኝ
ሲያባብለኝ ኖሮ፥ ‘አለኝ’ ብዬ ስለው ለዛሬ የሸጠኝ

ትናፍቂኛለሽ፣
እንደ ወደፊቱ፣ ምኞቴን በሙሉ እንደ‘ማሳካበት፣
ናፍቆትሽን ዘንግቼ እንደምስቅበት

ትናፍቂኛለሽ፣
ናፍቄ፣ ናፍቄ ያገኘሁሽ ለታ፥ ታናድጂኛለሽ፣
እኔ ግጥም ስጽፍ፣ ስቀኝልሽ ውለሽ፣
«የማነህ ሥራ ፈት፥ ‘ጎ ጌት ኤ ጆብ’» ብለሽ ታጣጥይኛለሽ!

LEAVE A REPLY