መንገዱን ክፈቱት ህጻኑ ይለፍበት ||| ህሊና ደሳለኝ

መንገዱን ክፈቱት ህጻኑ ይለፍበት ||| ህሊና ደሳለኝ

በአጉል ዘረኝነት ሰው ያመለካችሁ
መንገዱን ክፈቱት ተውኝ ልለፍበት
ተስፋ አለኝ ለነገ ልማር ልወቅበት
በሕጻን አእምሮ በንጹህ ወረቀት
ጥረት ብታደርጉም ክፋት ልትጽፉበት
ላጲሱ በእጀ ነው አገናዝባለሁ
መጥፎውን አጥፍቸ መልካም እጽፋለሁ
እንዲያውም ልመለስ መማሩንም ተውሁት
አነዴ ልለፍ እና ከእነ አካቴው ዝጉት

ያልተማሩ አባቶች ያቆዩትን ፍቅር
ዛሬ ላይ ሲያፈርሱት የዘመኑ ምሁር
ካልተማረው ይልቅ ያወቀው ካጠፋ
በዲያቢሎስ ትምህርት እኔስ ለምን ልልፋ?

አደብ እስክትገዙ ሰላም እስኪመጣ
አማናዊ ፈራጂ አጥፊን እስኪቀጣ
ተፈጥሮን በማድነቅ እንዲሁ እቆያለሁ
በእውነተኛ መምህር ያን ጊዜ እማራለሁ ።

LEAVE A REPLY