አንት የኔ ፈጣሪ! || ይመር ቦሩ

አንት የኔ ፈጣሪ! || ይመር ቦሩ

በመጥረቢያ አንገቴተቀልቶ ከሚወድቅ

ጥርሴ በመዶሻተወቅጦ ከሚደቅ

ራሴ በቋጥኝ ከሚፈጠፈጥ

እሳት ከሚያጋየኝበጎጆዬ ውስጥ

ሜንጫ ገጀራከምከተከት

ነፍስ ከማያውቁትከልጆቼ ፊት

ሞትን እያየሁትብዙእጥፍ ከምሞት

መንገድ ለመንገድከሚጎተት በድኔ

ፈርጦ ከሚወጣከአፎቱ ዓይኔ

ደሜ ቦይ ከሚቀድባፌ ተደፍቼ

በለው እንጂ አይዞህ የሚል ሰው አጥቼ

አርደው በቆርቆሮየትም ከሚጥ

ይበ ይመስልከሚዘለዝ

ሞት እንኳ ጨክኖ፣ ከሚዘገይብኝ

ቀለብ ከሚያረጉኝ፣ እንህያ ሬሳ

ላነር፣ ለቀበሮ፣ ለጅብ ጥንብ አንሳ

እጆቼን ዘርግቼዓይ አንጋጥጬ

ሃፍረቴን ሽጬ

የምለምንህ አንት የኔ ፈጣሪ

እንድትሰጠኝ ነውጨካኝ ያገር መሪ!

ግንእኩል የሚያሥርእኩል የሚገድል

ሽባ ሚያደርግሉን ዘር እኩል

እኩል ዓይን አውጥቶእኩል የሚያውር  

እኩል ሟጦዘርፎእርቃን የሚያስቀር

ወዳታች ዘቅዝቆእኩል የሚገርፍ

እኩል በኤሌትሪክየሚያንዘፈዝፍ

እኩል የሁሉን ጥፍርየሚነቅል በፒንሳ

እኩል የሚያኮላሽሳያልጥ ጎሣ

በወንድ ልጅ ብልትአንጠልጥሎ ኮዳ

እኩል የሚያስገፋየሥር ግድግዳ

እኩል የሚያሰቃይ

ቁም ስቅል የሚያሳይ

ያገሪቱን የዓለምን ሕግየሚጥስ ጧት ማታ

ፍርድ ሲገመድልየማያመነታ

ማእቀብና ዛቻፍፁም የማይፈራ

ፍትሃዊ ነኝ ብሎ ጭራሽ የሚኮራ

ሜጫንና ገጀራንየሚያደርግ ማረሻ

እንዲመረት ምርትየራብ ማስታገሻ

ብሔር ብሔረሰብየማያበላልጥ

እኩል የሚፈልጥእኩል የሚቆርጥ

የመረገጥ መብትን ዘጌቹ ሁላ

ኩል የሚያካፍልምንም ሳያዳላ

እኩል አፈር ድሜሁሉን የሚያስበላ

የሚገዛ አካልየሚረግጥ መሪ

አድለ እባክህአንት ፈጣሪ!

ምን ፍትህ ይገኛልከዚህ የበለጠ

ሜንጫ ከዱላሁሉም ካመለጠ

ኑሮ ውድነትያድርገኝ እምሽክሽክ

እንደጠፉ ይቅሩውሃና ኤለትሪክ

ጦሜን ዋል ልደርየምቀምሰው ልጣ

በሜንጫ፣ ገጀራአንገቴን ከማጣ

የመናገር መብቴተገፈፍኩ አልልም

ሰልፍ ተከለከልኩብዬ አላማርርም  

ምንም ሳልተነፍስአንገቴን ደፍቼ

ከገባሁ በሰላምከቤቴ ወጥቼ

በድንጋይ ክምርመንገ ሳይዘጋ

ኑሮን መኖር ከቻልኩበፍፁም ሳልሰጋ

ልጆቼን ካገኘሁከነአንገታቸው

እግራቸው ባለበትእንዲሁም እጃቸው

ሁሉም አካላቸውባለበት እስካለ

ከዚህ የበለጠምን ዲሞክራሲ አለ?

አይረግጡ እረግጦየሚገዛ መሪ

አጣህልኝ እንዴአንት የኔ ፈጣሪ?!

|| 11/05/2019 ||

LEAVE A REPLY