አሞራ || ማሕሙድ እንድሪስ

አሞራ || ማሕሙድ እንድሪስ

አስተውለህ ብታይ
እስኪ ወደ ሰማይ
ቀና በል ወደላይ
ለረዥሙ ጉዞ ሆኖ ባለአደራ
አቅጣጫውን ሳይስት ሰልፉን የሚመራ
ተመልከት አሞራ
ጊዜውን ጠብቆ በተከታዮቹ እየተቀየረ
ወዳለመለት ግብ መጓዝ ከጄመረ
የንፋሱን ግፊት
ሙቀትና ብርዱን በፅናት ይወጣል
ከዚያም ለተረኛው ቦታውን ይሰጣል
ከፊት መርቶ መርቶ
ያቅሙን አበርክቶ
ግዳጁን ጨርሶ ሲሰለፍ ከዃላ
ደሞ ባዲስ ጉልበት ይተካዋል ሌላ ።

LEAVE A REPLY