‘ርግጥ ነው || ገጣሚ ማሕሙድ እንድሪስ

‘ርግጥ ነው || ገጣሚ ማሕሙድ እንድሪስ

ላመት ባሉ ድምቀት ፍሪዳ ጥለናል
ለምለም ሳር ቄጤማ ጉዝጓዝ ጎዝጉዘናል
ፀአዳ ለብሰናል
የወል ተጋቢወች ሙሽሮች መስለናል ።

በቀለም ባበባ ተውቧል ቤታችን
በእንኳን አደረሰን
የምኞት መግለጫ — ደምቋል ሰፈራችን …

ሆኖም የፍቅርና የመግባባት እጦት
የወለደው ፍርሀት ደስታችንን ውጦት
ካውደ አመቱ በላይ ገዝፎ ስጋታችን
እያነቡ እስክስታ ሆኗል በአላችን ።

LEAVE A REPLY