ግቢው፣ ዩንቨርስቲው!! || አሥራደው ከፈረንሳይ

ግቢው፣ ዩንቨርስቲው!! || አሥራደው ከፈረንሳይ

እንዳልነበሩበትተናዳፊ ንቦች ፤
ሇህዝባቸው ጥቃትዘብ ቆሞ አዳሪዎች ፤
የዕውቀትን ጥበብትምህርት ቀስመውበት፤
ሇሇውጥ ሃዋሪያነትሃሳብ ላመኑበት፤
በአንድላይ ተነስተውእንዳልተመሙበት፤
ዘመን አሳልፎዘመንን ዯርቶ
ሳየው ይገርመኛል ግቢው አንቀላፍቶ
ግቢው አንኮራፍቶ። 
ፋኖ ተሰማራፋኖ ተሰማራ
እንዯነ ሚንእንዯ ጉቬራ
መሬት ላራሽ ይሁንገባርነት ይጥፋ
የድሃ ልጅ ይማርትምህርት ይስፋፋ ፤
ሃሳብን በሃሳብእያሞሻሇቅን፤
ትምህርት እንማርእንቅሰም እውቀትን። 
ማሇቱ ቀረና !
የአይምሮ ባዶነትየሃሳብ ድህነት፤
የህሊና ዝገትሃሞተ ቢስነት
ተዯማምረውበትጎሣ_ ዘረኝነት
ይታያል ተኝቶግቢው አንቀላፍቶ
ግቢው አንኮራፍቶ። 
የባዶነት ስሜትኳኳታ _ ኳኳታ
የውስጣዊ ቁሸትክርፋት _ ክርፋት ሽታ፤
ቂም በቀል ጥላቻተዯማምረውበት፤
ይታያል ተኝቶግቢው አንቀላፍቶ፤
ግቢው አንኮራፍቶ። 

LEAVE A REPLY