ቢደገምስ አቦ ! ? አድዋ እና አሽዋ || ማሕሙድ እንድሪስ

ቢደገምስ አቦ ! ? አድዋ እና አሽዋ || ማሕሙድ እንድሪስ

ስማ! !!

ደም አጥንት ህይወት ነው
ለጥቁር ዘር ሁሉ
የሰውነት ክብር በኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተሰዋ
ዘላለም የሚኖር
ዘመን የማይሽረው
ሁሌ ‘ሚያጣጥሙት የጀግንነት ፅዋ
ማንነትን ቀብሮ
ሀውልት በመገንባት
የሚለካ አይደለም !! አይነፃፅሩም አድዋና— አሽዋ ።
ስማ ! !
አስደናቂ እውነት ነው ክብሩ ማይደበዝዝ በግብዞች ተረክ
አድዋ ተግባር ነው አምሳያ የሌለው የጀግንነት መድረክ
በጨለማው ዘመን
ያፍሪካ ልጅ ሲባል— ህይወት ያለው እቃ
በግፍ ሲንገፈገፍ መከራ ሲቀበል ልክ የለሽ ሰቆቃ
የጥቁር ዘር ሁሉ
ሰውነቱ ታምኖ በኩልነት ክብር እንዲቆም ያበቃ
ፅልመትን የሻረ
አድዋ ብርሀን ነው ከከባድ እንቅልፉ አለምን ያነቃ ።

LEAVE A REPLY