ያ … ምትክ የለሽ ሰው || ማሕሙድ እንድሪስ

ያ … ምትክ የለሽ ሰው || ማሕሙድ እንድሪስ

ያ … ምትክ የለሽ ሰው ያ የጄግኖች አውራ
ያ … በድል ጎዳና ሀገሩን የመራ
ያ … የሚስቱ ሎሌ ትሁት አባወራ
ስለማይመጥነው
የሸመታ ሹመት ማዕረግ ድርደራ
መታሰቢያ እንዲሆን
ሁሉን አስተባብሮ
መክሮ ተመካክሮ ስለሰራው ስራ
ለማይሻር ክብሩ
ለመጠቀ ፍቅሩ
እምየ ተብሎ በሴት ስም ተጠራ።

LEAVE A REPLY