እስከ ዘለ አለም!!! || አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር)

እስከ ዘለ አለም!!! || አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር)

 

የፍቅር፡ የተስፋ እ’መቤት
የነጻነት ምንጭ፤ የደም ውጤት፡
ሰው የመሆን መለኪያ፡
የውበት ጥግ አምሳያ፡
የነጻነት ምልክት፡ መለያ፤
የማንነት መከታ ውቅር፡
የታሪክ ምሰሶ ማገር፤
ትከበሪያለሽ ሁሌም፡
ትዘከሪያለሽ በአለም፡
የድል ውጤት ነሽና፡
ትታወሻለሽ እንደገና፤
ደምቆ ያብባል ስምሽ፡
ህብር ድምቅ ነው ዝናሽ
አድዋ!
ክብርሽ ይታወስ ዛሬም
ይቀጥል… ነገና ከዚያም…

ደግሞም

እስከ ዘለ አለም… አለም፡፡

ፌብሪዋሪ 26/2015 ምሽት

LEAVE A REPLY