በህወሓት ፍርድ ቤት የሚመላለሱት ነብዮ ስሁል የብልፅግና የትግራይ ጽ /ቤት ሓላፊ ሆነው...

በህወሓት ፍርድ ቤት የሚመላለሱት ነብዮ ስሁል የብልፅግና የትግራይ ጽ /ቤት ሓላፊ ሆነው ተሾሙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በትግራይ የህወሓት ተፎካካሪ ሆኖ ብቅ ያለው ብልፅግና ፓርቲ  የታሪክ ጸሐፊውና ወያኔን በመታገል የሚታወቁትን  ነብዩ ስሑል ሚካኤልን ከመጋቢት 01/2012 ጀምሮ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽኀፈት ቤት ሓላፊ አድርጎ መሾሙን ዛሬ ይፋ አደረገ።

ፓርቲው ለሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ በጻፈው ደብዳቤ  ተመራጩ ነብዩ የተጣለባቸውን ሓላፊነት በትጋት እንዲፈፅሙም አሳስቧል። አቶ ነቢዮ ስሁልም ዛሬ በሰጡት መግለጫ በትግራይ የብልፅግና ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች ምደባ መካሄዱን ጠቁመው እርሳቸውም በተሰጣቸው ሓላፊነት በብቃት በማገልገል የትግራይን ሕዝብ ብልፅግና ለማሣደግ እንደሚተጉ አረጋግጠዋል።

በቀጣይ በመቀሌና በሌሎች የትግራይ ዞኖች እንዲሁም በአዲስ አበባ  የትግራይ ብልፅግና አባላትና አመራሮችን የማደራጀት ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

ነብዮ ስሁል አምባገነኑን የህወሓት ስርዓት አምርረው መተቸታቸውን ተከትሎ ለተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ተዳርገዋል።   ከወራት በፊት ህወሓት የትግራይ ሕዝብን ለአመፅ አነሳስተዋል በሚል ክስ መስርቶባቸው ለእስር ተዳርገው በዋስትና ወጥተዋል።  ክሳቸው ግን አሁንም በፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY