ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኮሮና ቫይረስ ከተያዘው ጃፓናዊ ጋር ንክኪ እንደነበራቸው የገለጹት የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተነገረ።
በሥራ ምክንያት ከ12 ቀናት በፊት ከጃፓናዊው ጋር ተደጋጋሚ ንኪኪ የነበራቸው 21 ሰዎች ነጻ መሆናቸውን በሐኪሞች እንደተገለጸላቸው ዶክተር ቶላ አስታውቀዋል። በጃፓናዊው ላይ ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘ ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ ለብቻቸው ተቀምጠው የነበሩት ዶክተር ቶላ በተደረገላቸው ምርምራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ታውቋል።
በቫይረሱ የተያዘው ጃፓናዊ ከእርሳቸው በተጨማሪ በአርሲ ዞን ሁለት ትምህርት ቤቶችን ሲጎበኙ ንኪኪ አላቸው የተባሉት ሁሉም ሰዎች እስካሁን ድረስ ባለው የጤንነታቸው ሁኔታ ነጻ መሆናቸው ተገልጿል።
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 5 ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው 992 ሰዎች ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት የጤና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ጉዳዮን አስመልክቶ መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ይፋ አድርጓል።