ከግብፅ በተቃራኒ የቆሙት ሱዳኖች ግድቡን በገንዘብ እንደግፋለን አሉ

ከግብፅ በተቃራኒ የቆሙት ሱዳኖች ግድቡን በገንዘብ እንደግፋለን አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በድርድሩ መሀል ከግብፅ አቋምና ከአሜሪካ ተፅዕኖ ያፈነገጡት ሱዳናዊያን ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታወቁ።

በቅርቡ ለግድቡ ግንባታ ገቢ ለማሰባሰብ በፕሬዚዳንት  ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ይፋ ተደርጎ ለተጀመረው መርሃ ግብር  ሱዳናውያን የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤትና ከአካባቢው ሀገራት ጋር በመተባበርና በመደጋገፍ የአባይ ተፋሰስን ከግጭት ቀጠናነት ይልቅ የዕድገት ማዕከል ለማድረግ እያከናወነች ያለውን ተግባር እንደሚደግፉም ሱዳናውያን አስታውቀዋል።

ሱዳኖች የግድቡ ግንባታ እስከሚጠናቀቅም የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑና ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዮን አስመልክቶ በቃል አቀባዮ በኩል ይፋ አድርጓል፡፡

LEAVE A REPLY