በአ/አ 24 መኖሪያ ቤቶች አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች ተገንብተው ተሰጡ

በአ/አ 24 መኖሪያ ቤቶች አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች ተገንብተው ተሰጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደርበሶስት ነጥብ 2 ሚዮን ብር ያስገነባቸውን 24 መኖሪያ ቤቶችአቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች አስረክቤያለሁ አለ፡፡

መኖሪያ ቤቶቹ በክፍለ ከተማው ወረዳ 13 በተለምዶ መብራትኃይል መጠለያ ከሚባለው ሰፈር የተገነቡ ናቸው፡፡ የክፍለከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ የቤቶቹንቁልፍ ለባለ ዕድለኞች አስረክበዋል፡፡

በመንግሥት ወጪ ግንባታው ተካሂዶ መኖሪያ ቤቱከተላለፈላቸው 24 ነዋሪዎች መካከል 6ቱ አካል ጉዳተኞችመሆናቸውን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረተሪያት ቢሮ ይፋአድርጓል፡፡ በስድስት ወር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተሰርተውየተጠናቀቁት ቤቶች እያንዳንዳቸው 24 ካሬ ሜትር ስፋትአላቸው፡፡ በከፍለ ከተማው የድሃ ድሃ ተብለው የተለዩ ከ15 ሺህበላይ ቤት ፈላጊዎች እንዳሉ እየተነገረ ነው

LEAVE A REPLY