ከአያቴ እስከ ‘ኔ || በማሕሙድ እንድሪስ

ከአያቴ እስከ ‘ኔ || በማሕሙድ እንድሪስ

አርበኛው አያቴ
ወራሪን ሲፋለም በዱር በገደሉ
ጃንሆይ ፋሽስትን ላውሮጳ ሊከሱ ሂደው ነበር አሉ
ከዚያ ሲመለሱ
ለድል አጥቢያ ጄግኖች ሹመት ሲለግሱ
ለባንዳ ላጎብዳጅ ክብር ሲያላብሱ
አያቴን ረሱ ።

አባቴና ደርጉ
ምክንያት አይሆን ምክንያት ምክንያት እያረጉ
ሲጋደሉ ኑረው
በመሀል ከተማ በየጥጋ ጥጉ
አልበቃ ብሏቼው,
ወደጠረፍ ዘምተው ሲዋጉ— ሲያዋጉ
በ”ቼ” ና “ሼ” ሰበብ እየተቧቀሱ
በምናምኒ”ዝም” እየተጫረሱ,
እኔን በጄርባዋ ያዘለች እናቴን ደም እንባ አስለቀሱ።”
አንዱ አንዱን ሊያጠፋ — ርስበርስ ሊጣፉ
እንደተሰለፉ እንደተጣደፉ ”
ሲባክኑ አለፉ ።”

የኔው ዘመን ደሞ
ዘመነ ራዕዩ ዘመነ ህዳሴ
በእኔነቴ ምክንያት በማንነት ውርሴ ”
በውልደቴ ሰበብ ተከፍቶልኝ ዶሴ ”
ይካስሰኝ ይዟል
ያራክሰኝ ይዟል
ያናክሰኝ ይዟል — ራሴን ከራሴ ።”
—”


— ልጄስ? ??

LEAVE A REPLY