ተመስገን እንበል || ዘ-ጌርሣም

ተመስገን እንበል || ዘ-ጌርሣም

ተመስገን  ፈጣሪ ሌላ ምን ይባላል

ሰው የሰጠው ቢሆን ዋጋ ያስከፍላል

ከምስጋና በቀር የማትፈልግ ሌላ

በአንድ ላይ ተንሰስተን እንግባ ምህላ

 

እናመስግን አንተን

ከፍ ከፍ አድርገን

እንባችን ይታበስ

ኢትዮጵያ ትወደስ

 

ከፍ ብላ በልፅጋ  በዓይናችን  ልናይ ነው

ችግሮች ሲጠፉ ትውልድ ደስ ሲለው

ውጡ እናመስግነው ወገኖች በሙሉ

የኢትዮጵያ ትንሣዔ ገሃድ ሁኗል አሉ

 

የአባይ ግድብ አልቆ መሞላት ጀምሯል

ምኞት የነበረው ይኸው በዓይን ታይቷል

የጨለማው ዘመን ሊገፈፍ ተቃርቧል

አኬሩን በእጃችን ቁጭ አድርጎልናል

እወቁበት ይላል የመጣልን ዕድል

ተግባብተን በመኖር እንድንሆን ድል በድል

 

ደህና ሁን ጨለማ ደህና ሁን ፅልመት

አባይ ሊያበራ ነው ከዓመት እስከ ዓመት

እልል በል ወገኔ በአራቱም ማዕዘናት

ደስታችን ታወጀ ተነገረ ብሥራት

የተጫወተብን ያ ጨለማ ዘመን

ገፈፍልን  ነው ልናየው በዓይናችን

 

እንኳን ደስ ላችሁ ኢትዮጵያውያን  በሙሉ

የአባይ ግድብ ሙሊት ዕውን ሁኗል አሉ

ተመስገን አምላኬ ተመስገን ድጋሜ

ይህን በማየቴ ሳልሞት በአካል ቁሜ

በማለት እንፀልይ እናመስግን ጌታን

ምስጋናም ይግባቸው ለዚህ ድል በቁን

 

በውሃ ሙሊት ብቻ አይቆምም ደስታችን

በአራቱም ማዕዘናት ሳትበራ አገራችን

ልናያት ቅርብ ነው አረንጓዴ ለብሳ

ለችግኝ ተከላው ሁሉም ከተነሳ

በልፅጊ አገራችን በረክተሽ ይሙላ

እኛም እንድንኖር በደስታ በተድላ

LEAVE A REPLY