ለምቾትህ ሲባል || በማሕሙድ እንድሪስ

ለምቾትህ ሲባል || በማሕሙድ እንድሪስ

ቅድም
ለምቾትህ ሲባል
አዝላህ በጄርባዋ ስትፈልጥ ነበረ
አሁን
ለምቾትህ ሲባል ቦታህ ተቀየረ
ጀርባዋን ተመልከት
በቁልል እንጨት ላይ መጥረቢያ ደርባ
እንዳትወዘውዝህ
እንዳትነቀንቅህ ተጨንቃ ተጠባ
ሳታርፍ ቁማለች
አንተ ምን አለብህ ? … ተመቻችተህ ጥባ ።
እማማ ስላንተ መች ይደክማትና
ይህን ሁሉ ሁና
እንዲህ እንዲህ ሁና
እቤትም አታርፍም
ማበሳሰያውን ትፈልጣለች ገና
ለዳቦው ለንጄራው ምጣድ ትጥድና
ለንፍሮው ለወጡ
ኧረ ምኑ ቅጡ … … … ምኑ ተነካና ???
ገና
ገና
ገና
አየሀት ይችን ሴት ?
አድገህ “ሰው” እስክትሆን ይሄው ነው ውሎዋ
ይሄው ነው ኑሮዋ
ከነ ድካሟና … … … … … ከነ ፈገግታዋ ።

ከዚያስ .… ?

LEAVE A REPLY