በኢትዮጵያ ተጨማሪ 521 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ 10 ሰዎች ሞተዋል

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 521 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ 10 ሰዎች ሞተዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– መስከረም 2 ቀን እለታዊ የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ባለፉት 24 ሰዐታት ለ8 ሺኅ 191ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 521 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

በተመሳሳይ ባለፋት 24 ሰዐታት ውስጥ የ10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ምክንያት ማለፉን ተከትሎ እስካሁን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 996 መድረሱ ታውቋል።
በአንጻሩ በትናንትናው ዕለት 469 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 24 ሺኅ 863 መድረሱን የጠቆመው የጤና ሚኒስቴር፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 63 ሺኅ 888 እንደደረሰ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY