በኢትዮጵያ አዲስ የሆነው የወረቀት አልባ ጉምሩክ አገልግሎት ዛሬ በይፋ ተመረቀ

በኢትዮጵያ አዲስ የሆነው የወረቀት አልባ ጉምሩክ አገልግሎት ዛሬ በይፋ ተመረቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ለሀገሪቱ የውጭ የንግድ ትስስርን በማገዝ ረገድ አስተዋጽዖው የጎላ ነው የተባለለለት የወረቀት አልባ ጉምሩክ አገልግሎት ዛሬ በይፋ ተመረቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙበት የወረቀት አልባ ጉምሩክ አገልግሎት፤ ኢትዮጵያ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ያላት የንግድ ትስስር እንዲጠናከር፣ የጋራ የድንበር አስተዳደር ሥርዓት በውጤታማነት እንዲከናወን፣ እንዲሁም በጉምሩክ እና በንግዱ ማኅረሰብ መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲፈጠር ያስችላል ተብሎለታል።
ከዚህ ባሻገር የመረጃ አስተዳደርና ልውውጥ ሥርዓትን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማዘመን ከመርዳቱ ባሻገር፤ በጉምሩክ ሥርዓት ሂደት ተጠያቂነት እና ግልጸኝነትን በመፍጠር፣ የሰነድ መጭበርበርን በማስቀረት ፍትሀዊ የንግድ ሥርዓት እንዲሰፍንም ድርሻ የጎላ መሆኑ ተገልጿል።
ለኢትዮጵያ አዲስ መንገድ የሆነው የወረቀት አልባ አገልግሎቱ ዛሬ በይፋ እንደጀመረም በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተነግሯል።

LEAVE A REPLY