ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አሜሪካ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሶማሊያ ውስጥ በፈፀመችው የአየር ድብደባ የገደለችውን የአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ከፍተኛ የጦር አዛዥ ማንነት ይፋ አደረገች፡፡
በወቅቱ በአሜሪካ ድብደባ የተገደለው አብዱልቃድር ኮማንዶስ የተሰኘ ግለሰብ እንደሆነም የቻይናው CGTN ዘግቧል።
ግለሰቡ በአልሸባብ ጽንፈኛ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የሓላፊነት ደረጃዎች እና በጦር አዛዥነት ያገለገለ እንደነበር ከአሜሪካ የወጣው መረጃ ያሳያል።
አብዱልቃድር ኮማንዶስ የተገደለው አሜሪካ በጁባ ላንድ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ፈፅማው በነበረ ድብደባ ሲሆን፤ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ የአልሸባብ ታጣቂዎችን በማሳደዱ እንገፋበታለን በማለት ተጨማሪ ጥቃት ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።